ዳዊትም መልእክተኛውን “እንዲህ ብለህ ለኢዮአብ ንገረው፦ በጦርነት ላይ ማን እንደሚሞት በቅድሚያ ስለማይታወቅ ‘አይዞህ በርታ’ በለው፤ ብስጭት እንዳያድርበትም ንገረው፤ ይልቁንም ኀይሉን አጠናክሮ አደጋ በመጣል ከተማይቱን እንዲይዝ አስጠንቅቀው” አለው።
2 ሳሙኤል 2:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አበኔርም፥ ኢዮአብን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ዘለዓለም ስንዋጋ እንኖራለንን? ፍጻሜውስ መራር መሆኑን አትገነዘብምን? ሰዎችህ እኛን ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንዲገቱ ትእዛዝ የማትሰጣቸው እስከ መቼ ነው?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አበኔር ኢዮአብን ጠርቶ፣ “ይህ ሰይፍ ዘላለም ማጥፋት አለበትን? ውጤቱ መራራ መሆኑን አንተስ ሳታውቀው ቀርተህ ነውን? ሰዎችህ ወንድሞቻቸውን ማሳደዱን እንዲያቆሙ ትእዛዝ የማትሰጣቸውስ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አበኔር ኢዮአብን ጠርቶ፥ “ሰይፍ በውኑ እስከ ዘለዓለም ያጠፋልን? ፍጻሜውሳ መራራ እንደሆነ አታውቅምን? ሰዎችህ ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንዲገቱ ትእዛዝ የማትሰጣቸውስ እስከ መቼ ነው?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርም ኢዮአብን ጠርቶ እንዲህ አለው፥ “ሰይፍ ለድል የምታጠፋ አይደለምን? ፍጻሜዋስ መራራ እንደ ሆነ አታውቅምን? ሕዝቡ ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ ይመለሱ ዘንድ ሕዝቡን የማትናገር እስከ መቼ ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርም ወደ ኢዮአብ ጮኸ፦ ሰይፍ በውኑ እስከ ዘላለም ያጠፋልን? ፍጻሜውሳ መራራ እንደ ሆነ አታውቅምን? ሕዝቡ ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ ይመለሱ ዘንድ ሕዝቡን የማትናገር እስከ መቼ ነው? አለው። |
ዳዊትም መልእክተኛውን “እንዲህ ብለህ ለኢዮአብ ንገረው፦ በጦርነት ላይ ማን እንደሚሞት በቅድሚያ ስለማይታወቅ ‘አይዞህ በርታ’ በለው፤ ብስጭት እንዳያድርበትም ንገረው፤ ይልቁንም ኀይሉን አጠናክሮ አደጋ በመጣል ከተማይቱን እንዲይዝ አስጠንቅቀው” አለው።
በዚህ ጊዜ አበኔር ኢዮአብን “ከእያንዳንዳችን ወገን ወጣቶችን መርጠን በጦር መሣሪያ ውጊያ በመግጠም ይወዳደሩ” አለው። ኢዮአብም “መልካም ነው” ሲል መለሰ።
እያንዳንዱ ሰው የባለጋራውን ራስ ይዞ ሰይፉን በጐኑ ሻጠበት፤ በዚህ ዐይነት ኻያ አራቱም ሰዎች በአንድነት ወድቀው ሞቱ፤ ስለዚህም በገባዖን የሚገኘው ያ ስፍራ “የሰይፍ ምድር” ተብሎ ተጠራ።
ኢዮአብም “አንተ ይህን ቃል ባትናገር ኖሮ የእኔ ሰዎች እስከ ነገ ጠዋት ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንደማይገቱ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ” ሲል መለሰለት።
ይህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የመረጠው ቀን ነው፤ እርሱ ዛሬ የበቀል እርምጃ ይወስዳል፤ ጠላቶቹንም ይቀጣል። የእርሱም ሰይፍ ብዙዎችን ይበላል፤ በደማቸውም ይለወሳል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኙ ምርኮኞቹን መሥዋዕት ያደርጋቸዋል።
“የግብጽ ከተሞች በሆኑት በሚግዶል፥ በሜምፊስ በጣፍናስ ይህን ቃል ዐውጅ፤ ‘ራሳችሁን ለመከላከል ተዘጋጁ፤ በዙሪያችሁ ያለው ሁሉ በጦርነት ይጠፋል።
በማግስቱም ሁለት እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኘና ሊገላግላቸው በመፈለግ ‘እናንተ ሰዎች፥ እናንተ ወንድማማች ናችሁ፤ ስለምን ትጣላላችሁ?’ አላቸው።