Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 17:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የጥል መነሻ መፍረስ እንደ ጀመረ ግድብ ነው፤ ስለዚህ ጥል ከማስከተሉ በፊት ክርክርን አቁም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ጠብ መጫር ግድብን እንደ መሸንቈር ነው፤ ስለዚህ ጠብ ከመጫሩ በፊት ከነገር ራቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፥ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 17:14
28 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ሁሉ ወደ ንጉሡ ቀርበው “ንጉሥ ሆይ! ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች አንተን ወስደው የራሳቸው ለማድረግ፥ እንዲሁም አንተንና ቤተሰብህን፥ ተከታዮችህንም ሁሉ አጅበው የዮርዳኖስን ወንዝ ለማሻገር መብት እንዳላቸው ስለምን ያስባሉ?” ሲሉ ጠየቁት።


አቢያና ሠራዊቱ እስራኤላውያንን ድል አድርገው ከፍ ያለ ጒዳት አደረሱባቸው፤ በዚህ ጦርነት ከእስራኤል አምስት መቶ ሺህ ምርጥ ወታደሮች ተገደሉ።


ትዕቢት ጠብን ያመጣል፤ ምክርን መጠየቅ ግን ብልኅነት ነው።


ትዕግሥተኛ ብትሆን አስተዋይ መሆንህን ትገልጣለህ፤ ቊጡ ብትሆን ግን ስንፍናህን ታሳያለህ።


ልዝብ አነጋገር ቊጣን ያስታግሣል፤ የቊጣ አነጋገር ግን ቊጣን ያባብሳል።


ኀይለኛ ከመሆን ይልቅ ታጋሽ መሆን ይሻላል፤ ብዙ ከተሞችን በጦርነት ድል ነሥቶ ከመያዝ ይልቅ ራስን መቈጣጠር ይበልጣል።


ኃጢአትን የሚወድ ጠብን ይወዳል፤ ከፍ ብሎ እንደ ተሠራ ደጃፍ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሰው ውድቀትን ይጋብዛል።


የቊጣን ስሜት መቈጣጠር አስተዋይነት ነው፤ ለበደለም ይቅርታ ማድረግ ጨዋነት ነው።


ማንኛውም ሞኝ ተቈጥቶ ጠብ ማነሣሣት ይችላል፤ ሰውን የሚያስከብረው ግን ከክርክር መራቅ ነው።


አንተ ከመሰከርክ በኋላ ሌላ ሰው ምስክርነትህ የተሳሳተ መሆኑን የገለጠ እንደሆን ስለምታፍር ስለ አየኸው ነገር ለመመስከር ፈጥነህ ወደ ሸንጎ አትሂድ።


ከሰል ፍምን፥ እንጨትም እሳትን እንደሚያበዛ ጠብ አጫሪ ሰው ጠብን ያባብሳል።


ቊጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ግልፍተኛም ብዙ በደልን ይፈጽማል።


የሚቻላችሁ ቢሆን ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የሚያስፈልገውን ሁሉ አድርጉ።


በጸጥታም ለመኖር እንድትጣጣሩ እና የራሳችሁን ጉዳይ እንድታስቡ ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁም በገዛ እጃችሁ እንድትሠሩ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos