2 ነገሥት 2:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም ወደ ቤትኤል ለመሄድ ከኢያሪኮ ተነሣ፤ በመንገድ ሳለ ከከተማይቱ በርከት ያሉ ልጆች ወጥተው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ “አንተ ራሰ መላጣ ከዚህ ውጣ!” እያሉ ጮኹበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድ ላይ ሲሄድ ሳለም ልጆች ከከተማ ወጥተው፣ “አንተ መላጣ፤ ውጣ! አንተ መላጣ ውጣ!” እያሉ አፌዙበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም ወደ ቤትኤል ለመሄድ ከኢያሪኮ ተነሣ፤ በመንገድ ሳለ ከከተማይቱ በርከት ያሉ ልጆች ወጥተው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ “አንተ ራሰ መላጣ ከዚህ ውጣ!” እያሉ ጮኹበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ልጆች ከከተማዪቱ ወጥተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌዙበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ብላቴኖች ከከተማይቱ ወጥተው “አንተ መላጣ፥ ውጣ! አንተ መላጣ፥ ውጣ!” ብለው አፌዙበት። |
እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።
በመንገድም ሳሉ ኤልያስ ኤልሳዕን “እነሆ፥ አንተ በዚህ ቈይ፤ እኔ ወደ ቤትኤል እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ከቶ ከአንተ አልለይም” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ቤትኤል ሄዱ።
እስራኤላውያን ግን በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሳለቁ፤ በነቢያቱም በማፌዝ፥ የእግዚአብሔርን ቃል አቃለሉ፤ ከዚህም የተነሣ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ በሕዝቡ ላይ ወረደ፤ ከታላቅ ቊጣውም ለማምለጥ አልቻሉም።
“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ ያነሱ ሰዎች ያፌዙብኛል፤ የእነርሱ አባቶች የበጎቼን መንጋ ከሚጠብቁ ውሾቼ ጋር እንኳ እንዲሰማሩ የምንቃቸው ሰዎች ነበሩ።
እናንተ ኃጢአተኞች በደልን የተሸከማችሁ ወገኖች! የክፉ አድራጊዎችም ትውልድ! ሕይወታችሁ የተበላሸ፥ እግዚአብሔርን የተዋችሁና የእስራኤልን ቅዱስ የናቃችሁ በእርሱም ላይ ጀርባችሁን ያዞራችሁ ናችሁ።
ሕዝቡም እርስ በርሱ አንዱ ሌላውን ለመጨቈን ባልንጀራ በባልንጀራው ላይ ይነሣሣል፤ ወጣቱ ሽማግሌውን አያከብርም፤ ተንቆ ይኖር የነበረውም ሰው ክብር ባለው ሰው ላይ ይታበያል።
እግዚአብሔር ሆይ! አታለልከኝ፤ እኔም ተታለልኩ፤ አንተ ከእኔ ትበረታለህ፤ ኀይልህም በእኔ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ሰው ሁሉ በየዕለቱ በማሽሟጠጥ ይዘባበትብኛል።
እኔ በምናገርበት ጊዜ ሁሉ የምናገረው ዐመፅንና ጥፋትን ነው፤ አምላክ ሆይ! አንተ ያዘዝከኝን የትንቢት ቃል በመናገሬ፥ እኔ ዘወትር እሰደባለሁ፤ መላገጫም ሆኛለሁ።
ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፤ አባቶች እሳት ያቀጣጥላሉ፤ ሴቶች ‘የሰማይ ንግሥት’ ለተባለችው ጣዖት ኅብስት ለመጋገር ሊጥ ያቦካሉ፤ እኔንም ለማስቈጣት ለሌሎች አማልክት የወይን ጠጅ መባ ያቀርባሉ።
የቤትኤል ከተማ ነዋሪዎች ሆይ! በሠራችሁት ከባድ ኃጢአት ምክንያት በእናንተም ላይ ይህንኑ የመሰለ ጥፋት ይደርስባችኋል፤ ጦርነቱም እንደ ተነሣ ጎሕ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ወዲያውኑ ይገደላል።”
በሰማርያ ከተማ የሚኖሩ ሕዝቦች በቤትአዌን ስላለው በጥጃ ምስል በተሠራ ጣዖት በታላቅ ፍርሀት ይርበደበዳሉ፤ ክብሩ ስለ ተገፈፈ ሕዝቡ ያለቅሳሉ፤ የጣዖቱ ካህናትም እሪ ብለው ይጮኻሉ።
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እናንተ ብታመነዝሩም እንኳ የይሁዳ ሕዝብ በደለኛ እንዲሆን አታድርጉ፤ ወደ ጌልጌላ ወይም ወደ ቤትአዌን አትሂዱ፤ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁም አትማሉ።
ስለ ሠሩት ኃጢአት የእስራኤልን ሕዝብ በምቀጣበት ቀን በቤትኤል የሚገኙትን መሠዊያዎች አፈራርሳለሁ፤ የመሠዊያዎቹም ቀንዶች ተሰባብረው በምድር ላይ ይወድቃሉ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደ ቤትኤል ሄዳችሁ ኃጢአት ሥሩ! ወደ ጌልጌላም ሂዱና የበለጠ በደል ፈጽሙ! በየዕለቱ መሥዋዕታችሁን አቅርቡ! በየሦስተኛውም ቀን ዐሥራታችሁን ስጡ።
ወደ ቤርሳቤህ አትሂዱ፤ ቤቴል ፈራርሳ እንዳልነበረች ስለምትሆን በጌልገላ የሚኖሩ ሕዝቦችም ስደት ስለ ተፈረደባቸው ወደ ቤቴልም ሆነ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ።”