Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የቤትኤል ከተማ ነዋሪዎች ሆይ! በሠራችሁት ከባድ ኃጢአት ምክንያት በእናንተም ላይ ይህንኑ የመሰለ ጥፋት ይደርስባችኋል፤ ጦርነቱም እንደ ተነሣ ጎሕ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ወዲያውኑ ይገደላል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ ቤቴል ሆይ፤ ክፋትሽ ታላቅ ስለ ሆነ፣ በአንቺም ላይ እንደዚሁ ይሆናል፤ ያ ቀን ሲደርስም፣ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ቤቴል ሆይ! ከኃጢአታችሁም ክፋት የተነሣ እንዲሁ ይደረግባችኋል፤ ጎሕ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ክፋት የተ​ነሣ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ጋም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ይጥ​ሉ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከኃጢአታችሁም ክፋት የተነሣ ቤቴል እንዲሁ ያደርግባችኋል፥ በነጋ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 10:15
8 Referencias Cruzadas  

አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአንድ ጊዜያዊ የቅጥር ሠራተኛ የሥራ ጊዜ እንደሚቋረጥ የሞአብ ክብርና ብዙ ሕዝቦችዋ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይዋረዳል፤ ከሕዝቧ የተረፉትም በጣም ጥቂቶችና ደካሞች ይሆናሉ።”


በሕዝባችሁ ላይ ከባድ ጦርነት ይመጣል፤ ምሽጎቻችሁ ሁሉ ይፈራርሳሉ፤ ይህም ንጉሥ ሸልማን የቤትአርቤልን ከተማ በጦርነት እንዳፈራረሰና እናቶችን ከልጆቻቸው ጋር በምድር ላይ ፈጥፍጦ እንደ ጨረሰበት ጊዜ ይሆናል።


ሕዝቡ “እግዚአብሔርን መፍራት ስለ ተውን ንጉሥ አጥተናል፤ ንጉሥ ቢኖረንስ ምን ያደርግልናል?” ይላሉ።


በሰማርያ ከተማ የሚኖሩ ሕዝቦች በቤትአዌን ስላለው በጥጃ ምስል በተሠራ ጣዖት በታላቅ ፍርሀት ይርበደበዳሉ፤ ክብሩ ስለ ተገፈፈ ሕዝቡ ያለቅሳሉ፤ የጣዖቱ ካህናትም እሪ ብለው ይጮኻሉ።


የሰማርያ ንጉሥ የውሃ ላይ ዐረፋ ሆኖ ይቀራል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን እስራኤልን ገና በሕፃንነቱ ወደድኩት፤ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት።


ታዲያ፥ ይህ መልካም የሆነው ነገር በእኔ ሞትን አመጣብኝ ማለት ነውን? አይደለም! ነገር ግን ኃጢአት፥ ኃጢአት ሆኖ እንዲገለጥ በመልካሙ ነገር አማካይነት ሞትን አመጣብኝ፤ ስለዚህ ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት የበለጠ ኃጢአተኛ ሆነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos