ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ ለመውለድ አለመቻሏን ባወቀች ጊዜ በእኅቷ ቀናችባት፤ ስለዚህ ያዕቆብን “ልጅ ስጠኝ፤ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው።
2 ቆሮንቶስ 7:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን ሐዘን ወደ መዳን የሚመራ በንስሓ የሚገኘውን ለውጥ ስለሚያስገኝ ጸጸትን አያስከትልም፤ ዓለማዊ ሐዘን ግን ሞትን ያመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን ወደ ድነት ለሚያደርስ ንስሓ ያበቃል፤ ጸጸትም የለበትም። ዓለማዊ ሐዘን ግን ለሞት ያበቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ወደ መዳን ለሚያደርስ ንስሓ ያበቃል፤ ጸጸትም የለበትም፤ ዓለማዊው ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ እግዚአብሔር ተብሎ የሚደረግ ኀዘን የዘለዓለም ሕይወትን የሚያሰጥ ንስሓ ነው። ስለ ዓለም የሚደረግ ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል። |
ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ ለመውለድ አለመቻሏን ባወቀች ጊዜ በእኅቷ ቀናችባት፤ ስለዚህ ያዕቆብን “ልጅ ስጠኝ፤ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው።
ዮናዳብ አምኖንን “አንተ የንጉሥ ልጅ ሆነህ ሳለ በየቀኑ ሰውነትህ ጠውልጎ የማይህ ስለምንድን ነው? እስቲ ንገረኝ” ሲል ጠየቀው። አምኖንም “የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን ስለ ወደድኩ ነው” ሲል መለሰለት።
አኪጦፌል የሰጠው ምክር ተቀባይነት እንዳላገኘ በተረዳ ጊዜ አህያውን ጭኖ ወደ መኖሪያ ከተማው ተመልሶ ሄደ፤ ሁሉን ነገር መልክ በማስያዝ ካስተካከለም በኋላ ተሰቅሎ ሞተ፤ በቤተሰቡም መቃብር ተቀበረ።
አክዓብ፥ የእዝራኤላዊው ናቡቴ “ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም!” ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም።
እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።”
የሸለቆ ርግቦች ራሳቸውን ለማዳን ወደ ተራራ እንደሚወጡ እንዲሁም ከሰዎቹ መካከል ከሞት የተረፉ ካሉ በተራራ ላይ ተገኝተው በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ ሸለቆ ርግቦች የሐዘን እንጒርጒሮ ያሰማሉ።
እግዚአብሔር የነነዌ ሰዎች ያደረጉትንና ከክፉ መንገዳቸው መመለሳቸውን ተመለከተ፤ ስለዚህም ራርቶላቸው በእነርሱ ላይ ሊያመጣ የነበረውን ቅጣት አልፈጸመም።
እግዚአብሔርም “ስለዚህች ቅል ልትበሳጭ ይገባሃልን?” አለው። ዮናስም “በእርግጥ መበሳጨት ይገባኛል፤ እንዲያውም በንዴት እስከምሞት ድረስ መበሳጨት አለብኝ!” አለ።
“ቀራጩ ግን በሩቅ ቆመና፥ ቀና ብሎ ወደ ሰማይ ለማየት እንኳ አልደፈረም፤ ነገር ግን በእጁ ደረቱን እየመታ፥ ‘አምላክ ሆይ! እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ!’ ይል ነበር።
እነርሱም ይህንን በሰሙ ጊዜ የሚመልሱትን አጥተው ዝም አሉ፤ “እንግዲህ እግዚአብሔር ለአሕዛብም ለአዲስ ሕይወት የሚያበቃቸውን ንስሓ ሰጥቶአቸዋል፤” በማለትም እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
እንደገና ወደ እናንተ ስመጣ አምላኬ ምናልባት በእናንተ ፊት ያዋርደኛል ብዬ እፈራለሁ፤ ከዚህ ቀደም ኃጢአት ሠርተው በዚሁ በሠሩት ርኲሰት፥ ዝሙትና፥ ስድነት ንስሓ ስላልገቡት ሰዎች ሐዘን ላይ እወድቃለሁ ብዬ እፈራለሁ።
አሁን ግን ደስ ብሎኛል፤ የተደሰትኩበትም ምክንያት እናንተን ስላሳዘንኳችሁ ሳይሆን በሐዘናችሁ ምክንያት ንስሓ ገብታችሁ በመለወጣችሁ ነው፤ እንግዲህ ሐዘናችሁ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ሆነ እኛ ምንም አልበደልናችሁም ማለት ነው።
በኋላም ዔሳው በረከትን እንደገና ለመቀበል በፈለገ ጊዜ ይህን በረከት እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ እያለቀሰ እንኳ ያንን በረከት ተግቶ ቢፈልግ ሊያገኘው አልቻለም። ለንስሓ ምንም ዕድል አላገኘም።
ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤