Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 18:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ጠንካራ መንፈስ ሕመምን ያስታግሣል፤ መንፈሱ የደከመውን ግን ማንም አይረዳውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በሕመም ጊዜ፣ ሰውን መንፈሱ ትደግፈዋለች፤ የተሰበረውን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የሰው ነፍስ ሕመሙን ይታገሣል፥ የተቀጠቀጠን መንፈስ ግን ማን ያጠንክረዋል?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ብልህ አገልጋይ የጌታውን ቍጣ ያበርዳል፥ አእምሮ የጐደለውን ሰው ማን ይችለዋል?

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 18:14
26 Referencias Cruzadas  

ሁሉን የሚችል አምላክ በፍላጻዎቹ ወግቶኛል፤ መርዛቸውም በሰውነቴ ተሠራጭቶአል፤ የሚያስደነግጥ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ዙሪያዬን ከቦኛል።


እኔ ድኻና ምስኪን ነኝ፤ የደረሰብኝም መከራ ልቤን አቊስሎታል።


ልባቸው የተሰበረባቸውን ይፈውሳል፤ ቊስላቸውንም ይጠግናል።


ከጠላቶቼ ዛቻ የተነሣ ፈርቼአለሁ፤ በክፉዎችም ጭቈና ደቅቄአለሁ፤ እነርሱ መከራን ያመጡብኛል፤ በቊጣና በጥላቻ ይመለከቱኛል።


ፍርሀትና ድንጋጤ ይዞኛል፤ መላ ሰውነቴም ተሸብሮአል።


ሙሴም ይህን ሁሉ ለእስራኤላውያን ነገረ፤ እነርሱ ግን በወደቀባቸው ጨካኝ ጭቈና ምክንያት መንፈሳቸው ተሰብሮ ስለ ነበረ ሊያዳምጡት አልፈለጉም።


የልብ ደስታ ፊትን ያበራል፤ የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ያደቃል።


ደስተኛነት ለልብ መልካም መድኃኒት ነው፤ የመንፈስ ሐዘንተኛ መሆን ግን አጥንትን ይሰብራል።


የምንመካበት ነገር ይህ ነው፤ ይህም እውነት መሆኑን ኅሊናችን ይመሰክርልናል፤ ከሌሎች ሰዎችና በተለይም ከእናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት ከእግዚአብሔር ባገኘነው ቅድስናና ቅንነት የተመሠረተ ነው፤ ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ጸጋ ነበር እንጂ በሰው ጥበብ አልነበረም።


ስለዚህ ይህ ሰው በጣም ከማዘኑ የተነሣ ተስፋ እንዳይቈርጥ ይልቅስ ይቅርታ እንድታደርጉለትና እንድታጽናኑት ይገባል።


ወንድሞቼ ሆይ! ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ ደስ የሚያሰኙ ነገሮችን እንዳገኛችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ።


ምንም እንኳ የተለያዩ ፈተናዎች ለጥቂት ጊዜ የሚያስቸግሩአችሁ ቢሆኑ በእርሱ ደስ ይበላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos