1 ጢሞቴዎስ 4:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለራስህና ለማስተማር ሥራህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ነገሮች ጽና፤ ይህን በማድረግም ራስህንና የሚሰሙህን ታድናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሕይወትህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፣ ራስህንና የሚሰሙህንም ታድናለህና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለራስህና ለምታስተምረው ትምህርት ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ነገሮች ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንና የሚሰሙህን ታድናለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና። |
እንዲህ የሚል መመሪያም ሰጣቸው፦ “ፍርድ በምትሰጡበት ጊዜ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን በመገንዘብ ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ፤ እናንተ የምትፈርዱት ሰውን ለማስደሰት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ነው።
በእኔ ጉባኤ ፊት ቆመው ቢሆንማ ኖሮ ቃሌን ለሕዝቡ ባወጁ ነበር፤ ጠማማ መንገዳቸውንና ክፉ አኗኗራቸውንም ትተው ወደ እኔ እንዲመለሱ ማድረግ በቻሉ ነበር።”
“እናንተም ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ሰዎች ለፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በየምኲራቡም ይገርፉአችኋል፤ ምስክር እንድትሆኑኝ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ለፍርድ ትቆማላችሁ።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።
እስከ ዛሬ ድረስ የእግዚአብሔር ርዳታ አልተለየኝም፤ ስለዚህ ለትንሹም ለትልቁም እየመሰከርኩ እዚህ ቆሜአለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ አስቀድመው እንዲህ ይሆናል ያሉትን ከመናገር በቀር ሌላ ምንም አልተናገርኩም።
ይህንንም ማድረጌ የሥጋ ዘመዶቼ የሆኑትን አይሁድ ለማስቀናት ነው፤ በዚህም ሁኔታ ምናልባት ከእነርሱ አንዳንዶቹን ለማዳን እችል ይሆናል በማለት ነው።
የዚህ ዓለም ሰዎች በገዛ ጥበባቸው እግዚአብሔርን ማወቅ እንዳይችሉ እግዚአብሔር በጥበቡ ዘጋባቸው፤ ነገር ግን እንደ ሞኝነት በሚቈጠረው እኛ በምናስተምረው ወንጌል የሚያምኑትን ለማዳን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል።
ከእንግዲህ ወዲህ በሰዎች የተንኰል ሽንገላና አታላይነት በተዘጋጀ በአሳሳች የትምህርት ነፋስና ሞገድ ወዲያና ወዲህ ተገፍትረው እንደሚወሰዱ ሕፃናት አንሆንም።
አሕዛብ የሚድኑበትን ቃል እንዳንናገር እንኳ ይከለክሉናል፤ በዚህ ዐይነት ኃጢአትን በኃጢአት ላይ እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ ስለዚህ በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቊጣ መጥቶባቸዋል።
ወደ መቄዶንያ ስሄድ ሳለሁ ዐደራ እንዳልኩህ እዚያ ያሉ አንዳንድ ሰዎች የሐሰት ትምህርት እንዳያስተምሩ ታደርጋቸው ዘንድ በኤፌሶን ተቀመጥ።
ይህን ትምህርት ለአማኞች ብታስገነዝብ የእምነትን ቃልና የምትከተለውን መልካም ትምህርት እየተመገብክ ያደግኽ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።
ስለዚህ እነርሱም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘውን መዳንና ዘለዓለማዊ ክብርን እንዲያገኙ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሰዎች ስል ሁሉን ነገር እታገሣለሁ።
እነሆ እኔ ጳውሎስ “ዕዳውን እከፍልሃለሁ” ብዬ በገዛ እጄ ጽፌ አረጋግጥልሃለሁ፤ ሆኖም ስለ ሕይወትህ አንተ ራስህ እንኳ የእኔ ባለዕዳ መሆንክን እኔ ላስታውስህ አያስፈልግም።
ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ተጠንቀቁ፤ እንዲሁም ምንም መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይበቅልና እንዳያስቸግራችሁ ብዙዎችንም እንዳያረክስ ተጠንቀቁ።
ባልተለመደ በልዩ ልዩ ዐይነት ትምህርት አትማረኩ፤ ልባችን የመብል ሥነ ሥርዓቶችን በመጠበቅ ሳይሆን በጸጋ ቢጸና መልካም ነው፤ ይህን የምግብ ሥነ ሥርዓት የተከተሉ ሰዎች ምንም አልተጠቀሙም።