Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 19:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እንዲህ የሚል መመሪያም ሰጣቸው፦ “ፍርድ በምትሰጡበት ጊዜ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን በመገንዘብ ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ፤ እናንተ የምትፈርዱት ሰውን ለማስደሰት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እንዲህም አላቸው፤ “እናንተ የምትፈርዱት ለሰው ሳይሆን፣ ፍርድ በምትሰጡበት ጊዜ ሁሉ ከእናንተ ጋራ ለሆነው ለእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ በምትሰጡት ውሳኔ ሁሉ ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፈራጆቹንም እንዲህ አላቸው፦ “ለጌታ እንጂ ለሰው አትፈርዱምና፥ እርሱም በፍርድ ነገር ከእናንተ ጋር ነውና የምታደርጉትን ልብ ብላችሁ ተገንዘቡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ፈራ​ጆ​ቹ​ንም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ ለሰው አት​ፈ​ር​ዱ​ምና፥ የፍ​ር​ድም ነገር ከእ​ና​ንተ ጋር ነውና የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ተመ​ል​ከቱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ፈራጆቹንም “ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አትፈርዱምና፥ እርሱም በፍርድ ነገር ከእናንተ ጋር ነውና የምታደርጉትን ተመልከቱ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 19:6
10 Referencias Cruzadas  

ቤተ መቅደሱን ትሠራለት ዘንድ እግዚአብሔር አንተን እንደ መረጠህ አትዘንጋ፤ አሁንም በርትተህ በቈራጥነት ሥራው።”


በአንድ አገር ግፍ ሲሠራና መብት በመንፈግ ፍትሕ ሲጓደል ባየህ ጊዜ አትደነቅ፤ እያንዳንዱ ገዥ የበላይ ተመልካች አለው፤ ከሁሉም በላይ የሆነ ሌላ ተመልካች ደግሞ አለ።


“የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት።


ቀጥሎ ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ “የሰው ሕይወት በሀብቱ ብዛት አይደለም፤ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ከስስትም ተጠበቁ።”


ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ! ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ! እነሆ፥ ጊዜው ቀርቦአል!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እነርሱን አትከተሉአቸው።


የመቶ አለቃው ይህን በሰማ ጊዜ ወደ አዛዡ ሄደና “ምን ልታደርግ ነው? ይህ ሰው እኮ የሮም ዜጋ ነው!” አለው።


ከዚህ በኋላ የሸንጎውን አባሎች እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ! በእነዚህ ሰዎች ላይ በምታደርጉት ነገር ተጠንቀቁ።


በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’


ሙሴ የሰጣችሁን ሕግና ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ ይኸውም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ውደዱ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ ትእዛዙንም ጠብቁ፤ ለእርሱም ታማኞች ሆናችሁ በሙሉ ልባችሁ፥ በፍጹም ሐሳባችሁ አገልግሉት።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos