በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እንዲህ ሲል ላባን በቊጣ ቃል ተናገረው፤ “ታዲያ፥ የፈጸምኩት በደል ምንድን ነው? እስቲ ምን አጥፍቼ ነው እንዲህ የምታሳድደኝ?
1 ሳሙኤል 20:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታንም፣ “ለምን ይገደላል? ጥፋቱስ ምንድን ነው?” ሲል አባቱን ጠየቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል፥ “ስለ ምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል፦ ስለ ምን ይሞታል? ያደረገውስ ምንድር ነው? ብሎ መለሰለት። |
በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እንዲህ ሲል ላባን በቊጣ ቃል ተናገረው፤ “ታዲያ፥ የፈጸምኩት በደል ምንድን ነው? እስቲ ምን አጥፍቼ ነው እንዲህ የምታሳድደኝ?
የሁሉም ዕድል ፈንታው አንድ ዐይነት ነው፤ ይህም በዓለም እንደሚደረገው እንደማንኛውም ነገር ሁሉ እጅግ የከፋ ነው፤ ሰዎችም በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አእምሮአቸው በክፋትና በእብደት የተሞላ ሆኖ በመጨረሻ ይሞታሉ።
ጲላጦስም ሦስተኛ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ሰው ያደረገው በደል ከቶ ምንድን ነው? እኔ ለሞት የሚያደርስ ምንም ነገር አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ገርፌ እለቀዋለሁ።”
“መትቼ ከግድግዳ ጋር አጣብቀዋለሁ!” ብሎ በልቡ አሰበ፤ ከዚህም በኋላ ጦሩን በዳዊት ላይ ሁለት ጊዜ ወረወረ፤ ዳዊት ግን ሁለቴም ዞር እያለ አመለጠ።
ዮናታንም ዳዊትን በማመስገን ለሳኦል እንዲህ ሲል ነገረው፤ “በአገልጋይህ በዳዊት ላይ ክፉ ነገር አታድርግ፤ እርሱ ምንም ነገር አልበደለህም፤ ይልቅስ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ታላቅ ጥቅም በማስገኘት ረድቶሃል፤
እርሱ ለሕይወቱ ሳይሳሳ በመጋፈጥ ጎልያድን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም ይህን ባየህ ጊዜ ደስ ብሎህ ነበር፤ ታዲያ አሁን አንተ በንጹሕ ሰው ላይ በደል ለመሥራት ስለምን ታስባለህ? ምክንያት በሌለውስ ነገር ዳዊትን ለመግደል ስለምን ፈለግኽ?”
ከዚህ በኋላ ዳዊት በራማ ከምትገኘው ከናዮት በመሸሽ ወደ ዮናታን ሄዶ “ከቶ ምን አደረግሁ? ምንስ ወንጀል ፈጸምኩ? አባትህ ለመግደል የሚፈልገኝስ ምን በድየው ነው?” ሲል ጠየቀው።
አቤሜሌክም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ዳዊት ለአንተ የታመነ የጦር መኰንን ነው፤ የአንተው የራስህ ዐማች ከመሆኑም ሌላ የክብር ዘብህ አዛዥ ነው፤ በቤተ መንግሥትህም አደባባይ እንደ እርሱ የሚከበር ማን አለ?