አስቴርም “ጠላታችንና ሞት የፈረደብንማ ሃማን የተባለው ይህ ክፉ ሰው ነው!” አለችው። ሃማንም እጅግ በመደንገጥ አንዴ ወደ ንጉሡ፥ አንዴ ወደ ንግሥቲቱ ይመለከት ነበር፤
1 ጴጥሮስ 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙሪያችሁ ይንጐራደዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሳችሁን የምትገዙ ሁኑ፣ ንቁም፤ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ዙሪያውን ይንጐራደዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጠን ኑሩ፤ ንቁም፤ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ |
አስቴርም “ጠላታችንና ሞት የፈረደብንማ ሃማን የተባለው ይህ ክፉ ሰው ነው!” አለችው። ሃማንም እጅግ በመደንገጥ አንዴ ወደ ንጉሡ፥ አንዴ ወደ ንግሥቲቱ ይመለከት ነበር፤
መሪዎቻቸው፥ በገደሉአቸው እንስሶች ዙሪያ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፤ ሕዝቡንም በጭካኔ ይገድላሉ፤ ገንዘብም ሆነ ሌላ ንብረት ያገኙትን ሁሉ ይወስዳሉ፤ በግድያቸውም ብዙዎችን ሴቶች ያለ ባል አስቀርተዋል።
ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
ግልገሎችዋ የተወሰዱባት ድብ እንደምታደርግ እኔም አደጋ እጥልባችኋለሁ፤ እቦጫጭቃችሁማለሁ፤ እንደሚባላ አንበሳ እሆንባችኋለሁ፤ እንደሚበጣጥስ ክፉ አውሬም እበጣጥሳችኋለሁ።
እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በኢየሩሳሌም ሆኖ፥ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ለእስራኤል መጠጊያ ምሽግ ይሆናል፤
አሞጽ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ሆኖ እንደሚያገሣ አንበሳ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ቃሉም ከኢየሩሳሌም ያስተጋባል፤ እረኞች መንጋ የሚያሰማሩበት መስክ ይጠወልጋል፤ በቀርሜሎስ ተራራ የሚገኘውም ልምላሜ ይደርቃል።”
አንበሳ በደን ውስጥ ዐድኖ የሚበላውን ሳያገኝ በከንቱ ያገሣልን? የአንበሳ ደቦልስ አንዳች ነገር ዐድኖ ሳይዝ በሚኖርበት ቦታ ድምፁን ያሰማልን?
እረኞች ለምለም የሆነ መሰማሪያቸው ስለ ወደመ “ዋይ!” እያሉ ሲያለቅሱ ስሙ፤ የዮርዳኖስን ወንዝ ተከትሎ ያለው የደን መኖሪያቸው ስለ ተደመሰሰ፥ አንበሶች በሐዘን ሲያገሡ ስሙ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ በራእይ አሳየኝ፤ ሰይጣንም ኢያሱን ለመክሰስ በስተቀኙ ቆሞ ነበር።
ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!
ቃሉ በተዘራ ጊዜ በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል የሚወስድባቸውን ሰዎች ነው።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ስምዖን! ስምዖን! እነሆ፥ ገበሬ ስንዴውን ከገለባ አበጥሮ እንደሚለይ እንዲሁም ሰይጣን እናንተን ሊያበጥራችሁ ፈለገ።
እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል።
እንዲሁም ሴቶች ጠጒርን በማሳመር ወይም በወርቅ ወይም በዕንቊ ወይም ውድ በሆነ ልብስ በማጌጥ ሳይሆን በማፈርና በትሕትና ተገቢ የሆነ የጨዋ ልብስ ይልበሱ።
ስለዚህ አንድ ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) ነቀፋ የሌለበት፥ አንዲት ሚስት ብቻ ያገባ፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚገዛ፥ በሥርዓት የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ችሎታ ያለው፥
ይልቅስ እንግዳ ተቀባይ፥ መልካም የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ ትክክለኛ፥ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ፥ በመጠን የሚኖር ይሁን።
ከዚህ በኋላ አንድ ታላቅ ድምፅ ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “እነሆ አዳኝነት፥ ኀይል፥ መንግሥትም የአምላካችን ሆኖአል! ሥልጣንም የመሲሑ ሆኖአል! ወንድሞቻችንን በአምላካችን ፊት ቀንና ሌሊት ሲያሳጣቸው የነበረ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአል፤
ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ ዲያብሎስ በታላቅ ቊጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና ምድርና ባሕር ወዮላችሁ!”
ታላቁም ዘንዶ ወደታች ተጣለ፤ እርሱ መላውን ዓለም የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።
ያሳታቸው ዲያብሎስ፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት በዲን በሚቃጠል እሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ፤ በዚያም ሌሊትና ቀን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሠቃያሉ።
ከዚህ በኋላ ሶምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ፤ እዚያም በወይን ተክል ውስጥ አልፈው ሲሄዱ አንድ ደቦል አንበሳ እያገሣ መጣበት፤