እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል በርትተን እንዋጋ! እንግዲህ ሁሉ ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!”
1 ቆሮንቶስ 16:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንቁ፤ በእምነት ጸንታችሁ ቁሙ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትጉ፤ በሃይማኖትም ቁሙ፤ ታገሡ ጽኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ። |
እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል በርትተን እንዋጋ! እንግዲህ ሁሉ ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!”
ፈሪ ልብ ላላቸው “እነሆ አምላካችሁ ጠላቶቻችሁን ለመበቀልና የበደላቸውንም ዋጋ ለመክፈል መጥቶ ስለሚያድናችሁ በርቱ! አትፍሩ!” በሉአቸው።
እርሱም “አንተ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደድክ ሰው ሆይ! መልካም ይሆንልሃል፤ አትፍራ! አይዞህ በርታ!” አለኝ። እርሱም በተናገረኝ ጊዜ ብርታት አገኘሁና “ጌታዬ ሆይ፥ ብርታት ስለ ሰጠኸኝ እነሆ፥ ተናገር” አልኩት።
ንጉሡ ቀደም ብለው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን የካዱትን ሁሉ በማታለል የእነርሱን ድጋፍ ያገኛል፤ እግዚአብሔርን በሚገባ የሚያውቁ ሰዎች ግን ይበረታሉ፤ ንጉሡንም አጥብቀው ይቃወሙታል።
አሁን ግን ዘሩባቤል ሆይ! በርታ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ! በርታ፤ የሀገሪቱ ሕዝብ ሆይ! በርቱ! እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ። እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ።
በሕዝቦች ዘንድ እንደ ርግማን ትቈጠሩ የነበራችሁት እናንተ የይሁዳና የእስራኤል ሕዝቦች ሆይ! እኔ አድናችኋለሁ፤ ለበረከትም ትሆናላችሁ፤ ስለዚህ አትፍሩ! በርቱ።”
“ለሠራዊት አምላክ ቤተ መቅደስን እንደገና ለመሥራት መሠረት በተጣለበት በቅርብ ጊዜ የነበሩ ነቢያት የተናገሩትን ቃል የሰማችሁ እናንተ አይዞአችሁ በርቱ!
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።
እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ የክርስቶስን ወንጌል የሚያስመሰግን ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁም ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ ዓላማ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ወንጌልን በኅብረት ለማዳረስ መጋደላችሁን እሰማለሁ።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።
የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በመንፈሳዊ ሕይወት በማደግ ጸንታችሁ እንድትቆሙና የእግዚአብሔርንም ፈቃድ በሙሉ እንድትፈጽሙ እርሱ ስለ እናንተ በጸሎቱ ዘወትር ይጸልያል።
የእምነትን መልካም ጦርነት ተዋጋ፤ አንተ ወደ እርሱ በተጠራህ ጊዜ በብዙ ምስክሮች ፊት ትክክለኛ ምስክርነትን የሰጠኸውን ዘለዓለማዊውን ሕይወት ያዝ።
“እነሆ! እኔ እንደ ሌባ በድንገት እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይሆንና ኀፍረቱን ሰዎች እንዳያዩበት ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው የተመሰገነ ነው!”
ፍልስጥኤማውያን ሆይ! እንግዲህ በርቱ! ጠንክሩ! ይህ ካልሆነ ቀድሞ እነርሱ የእኛ ባሪያዎች እንደ ነበሩ ሁሉ እኛም ደግሞ የዕብራውያን ባርያዎች ሆነን መቅረታችን ነው፤ ስለዚህ በወንድነት ጠንክራችሁ ተዋጉ!”