መዝሙር 58:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቃን በቀልን ባዩ ጊዜ ደስ ይላቸዋል፤ እግራቸውንም በግፈኞች ደም ይታጠባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኞችን ሲበቀልላቸው በማየታቸው ጻድቃን ደስ ይላቸዋል፤ በክፉዎችም ደም እግሮቻቸውን ይታጠባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአምላኬ ይቅርታው ይድረሰኝ አምላኬ በጠላቶቼ ላይ አሳየኝ። |
“የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና፥ እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።”
የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስና እስከ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ድረስ የሚርቅ ደም ከመጥመቂያው ወጣ።
አቤቱ፥ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፥ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኃይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፥ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።