Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 58:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የአ​ም​ላኬ ይቅ​ር​ታው ይድ​ረ​ሰኝ አም​ላኬ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አሳ​የኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጻድቃን በቀልን ባዩ ጊዜ ደስ ይላቸዋል፤ እግራቸውንም በግፈኞች ደም ይታጠባሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኃጢአተኞችን ሲበቀልላቸው በማየታቸው ጻድቃን ደስ ይላቸዋል፤ በክፉዎችም ደም እግሮቻቸውን ይታጠባሉ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 58:10
16 Referencias Cruzadas  

ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ያዩ ይጨ​ልሙ፥ ጀር​ባ​ቸ​ውም ዘወ​ትር ይጉ​በጥ።


አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ልዑል ነህ፤


ትል​ም​ዋን አር​ካው፥ መከ​ሯ​ንም አብ​ጀው፤ በነ​ጠ​ብ​ጣ​ብ​ህም ደስ ብሏት ትበ​ቅ​ላ​ለች


በጻድቃን ደግነት ከተማ ትቀናለች፥ በክፉዎችም ጥፋት ደስ ይላታል።


ሰማ​ያት ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መላ​እ​ክት ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። አሕ​ዛ​ብም ከሕ​ዝቡ ጋር ደስ ይላ​ቸ​ዋል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ሁሉ እርሱ ጽኑዕ ነው ይላሉ፤ የል​ጆ​ቹን ደም ይበ​ቀ​ላ​ልና፥ ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ይበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ልና፥ ለሚ​ጠ​ላ​ቸ​ውም ፍዳ​ቸ​ውን ይከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ዝ​ቡን ምድር ያነ​ጻል።”


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


መድ​ኀ​ኒ​ትን ከጽ​ዮን ለእ​ስ​ራ​ኤል ማን ይሰ​ጣል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ዝ​ቡን ምርኮ በመ​ለሰ ጊዜ፥ ያዕ​ቆብ ደስ ይለ​ዋል እስ​ራ​ኤ​ልም ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።


ቅቤ በመ​ን​ገዴ ይፈ​ስስ በነ​በረ ጊዜ፥ ወተት በተ​ራ​ራዬ ይፈ​ስ​ስ​ልኝ በነ​በረ ጊዜ።


ጻድ​ቃ​ንም አይ​ተው ሳቁ፤ ንጹ​ሓ​ንም በን​ቀት ይዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ዋል።


አቤቱ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ እን​ዲሁ ይጥፉ፤ ወዳ​ጆ​ችህ ግን ፀሐይ በኀ​ይሉ በወጣ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ሆን፤ እን​ዲሁ ይሁኑ። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።


የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ።


ኃጥእ እንደ ዐውሎ ነፋስ ኅልፈት ይጠፋል፤ ጻድቅ ግን ተሰውሮ ለዘለዓለም ይድናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios