መዝሙር 129:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዕርገት መዝሙር። እስራኤል፦ “ከትንሽነቴ ጀምሮ አብዝተው አጠቁኝ” ይበል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል እንዲህ ይበል፦ “ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወጣትነቴ ጀምሮ አደጋ ደርሶብኛል፤ እስራኤላውያን እንዲህ ይበሉ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ። |
ፈርዖንም፦ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ዓባይ ወንዝ ጣሉት፥ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት እንድትኖር ተዉአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
“ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮዎች ላይ አውጅ፥ እንዲህም በል፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ጽኑ ፍቅር የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስታውሼዋለሁ።
ጋሜል። ይሁዳ ስለ መጨነቅና ስለ ባርነት ብዛት ተማረከች፥ በአሕዛብ መካከል ተቀመጠች ዕረፍትም አላገኘችም፥ የሚያስጨንቁአት ሁሉ ተጨንቃ አገኙአት።
በበኣሊም የበዓል ቀኖች ዕጣን ለእነርሱ በማጠንዋና ራስዋን በጉትቾችዋና በጌጥዋ በማስጌጥ ውሽሞችዋን ተከትላ እኔን በመርሳትዋ እቀጣታለሁ፥ ይላል ጌታ።
እስራኤላውያን ለውጊያ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ አስቀድሞ በእነርሱ ላይ እንደተናገረውና እንደማለው እንዲሸነፉ የጌታ እጅ ትከፋባቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እጅግ ተጨነቁ።
ጌታ በእስራኤላውያን ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ስለዚህ ለመስጴጦምያ ንጉሥ ለኩሽን-ሪሽዓታይም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እስራኤላውያንም ለኩሽን-ሪሽዓታይም ስምንት ዓመት በባርነት ተገዙለት።
በመላው የእስራኤል ምድር ብረት አቅልጦ ሠሪ አይገኝም ነበር፤ ምክንያቱም ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር ነው።