Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 125 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


1 የዕርገት መዝሙር።

1 የዕርገት መዝሙር። በጌታ የታመኑ እንደማይታወክ ለዘለዓለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።

2 ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ፥ ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም ጌታ በሕዝቡ ዙሪያ ነው።

3 ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ የክፉዎች በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም።

4 አቤቱ፥ ለመልካሞች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።

5 ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዓመፅን ከሚሠሩት ጋር ጌታ ይወስዳቸዋል። ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos