Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 126 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


1 የዕርገት መዝሙር።

1 የዕርገት መዝሙር። ጌታ የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ሕልም የምናይ መስሎን ነበር።

2 በዚያን ጊዜ አፋችን በሳቅ፥ አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፥ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ፦ ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ።

3 ጌታ ለኛ ታላቅ ነገርን አደረገልን፥ ደስም አለን።

4 አቤቱ፥ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ።

5 በዕንባ የሚዘሩ በእልልታ ይለቅማሉ።

6 መሄድስ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፥ መመለስስ፥ ነዶአቸውን ተሸክመው በእልልታ ይመጣሉ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos