Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሆሴዕ 11:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “እስራኤል ገና ሕፃን ሳለ ወደድሁት፤ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን እስራኤልን ገና በሕፃንነቱ ወደድኩት፤ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እስ​ራ​ኤል ሕፃን በነ​በረ ጊዜ ወደ​ድ​ሁት፤ ልጄ​ንም ከግ​ብፅ ጠራ​ሁት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 11:1
18 Referencias Cruzadas  

ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ፥ ይህም ከጌታ ዘንድ በነቢይ “ልጄን ከግብጽ ጠራሁት” የተባለው እንዲፈጸም ነው።


ፈርዖንንም ትለዋለህ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እስራኤል የበኩር ልጄ ነው፤


እኔ ግን ጌታ፥ ከግብጽ ምድር ጀምሬ አምላክህ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ የለም።


በበኣሊም የበዓል ቀኖች ዕጣን ለእነርሱ በማጠንዋና ራስዋን በጉትቾችዋና በጌጥዋ በማስጌጥ ውሽሞችዋን ተከትላ እኔን በመርሳትዋ እቀጣታለሁ፥ ይላል ጌታ።


“ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮዎች ላይ አውጅ፥ እንዲህም በል፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ጽኑ ፍቅር የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስታውሼዋለሁ።


ወድጃችኋለሁ ይላል ጌታ፤ እናንተ ግን፦ “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል ጌታ። ሆኖም ያዕቆብን ወደድኩት።


ያዕቆብ ወደ አራም ምድር ሸሸ፥ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፥ ስለ ሚስትም በጎችን ያሰማራ ነበረ።


በአንቺም በኩል አለፍሁ፥ በደምሽም ውስጥ ስትንፈራገጪ አየሁሽ። በደምሽ እንዳለሽ በሕይወት ኑሪ አልሁሽ፥ አዎን በደምሽ ውስጥ እያለሽ በሕይወት ኑሪ አልሁሽ።


ጌታ የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ስለ በዛችሁ አይደለም፥ ይልቁንም እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ጥቂቶች ነበራችሁ፤


ኤፍሬምም፦ “በእውነት ባለ ጠጋ ሆኜአለሁ፥ ሀብትንም አግኝቻለሁ፥ በድካሜም ሁሉ ኃጢአት የሚሆን በደል አያገኙብኝም” አለ።


እንዲያገለግለኝ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኩር ልጅህን እገድላለሁ።’”


የዕርገት መዝሙር። እስራኤል፦ “ከትንሽነቴ ጀምሮ አብዝተው አጠቁኝ” ይበል፥


“ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ ነፍሴም የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።


ቤቴል ሆይ! ከኃጢአታችሁም ክፋት የተነሣ እንዲሁ ይደረግባችኋል፤ ጎሕ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።


በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንዴት እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።


በእርግጥ ሕዝቡን ይወዳል፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጁ ናቸው፤ እነርሱም በእግሮችህ ሥር ይሰግዳሉ፤ መመሪያህንም ከአንተ ይቀበላሉ።


በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ፥ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ።


በርኩሰቶችሽ ሁሉና በአመንዝራነትሽ ዕርቃንሽን ሆነሽ ተራቁተሽም በደምሽ ውስጥ ስትንፈራገጪ የነበርሽበት የልጅነትሽን ጊዜ አላስታወስሺም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios