ዳዊትም በዚያ ለጌታ መሠዊያ ሠራ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት አቀረበ፥ ጌታንም ጠራ፤ ጌታም ከሰማይ የሚቃጠለው መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት።
ዘሌዋውያን 3:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ቁርባኑም የአንድነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከበሬ መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በጌታ ፊት ያቅርብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ማንኛውም ሰው የሚያቀርበው ቍርባን ከላሞች መንጋ የሚቀርብ የኅብረት መሥዋዕት ከሆነ፣ እንከን የሌለበትን ተባዕት ወይም እንስት በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንኛውም ሰው ከቀንድ ከብቱ ለእግዚአብሔር የአንድነት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ነውር የሌለበትን አንድ ኰርማ ወይም ላም መርጦ ያምጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ቍርባን የደኅንነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከላሞች መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍርባኑም የደኅንነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከላሞች መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ። |
ዳዊትም በዚያ ለጌታ መሠዊያ ሠራ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት አቀረበ፥ ጌታንም ጠራ፤ ጌታም ከሰማይ የሚቃጠለው መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት።
ከአፈርም መሠዊያ ሥራልኝ፥ የሚቃጠለውንና የሰላም መሥዋዕትህን በጎችህንም በሬዎችህንም ሠዋበት፤ ስሜን በማሳስብበት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባርክሃለሁ።
የማንሣት ቁርባን ነውና ከእስራኤል ልጆች ዘንድ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የሰላም መሥዋዕታቸው የማንሣት ቁርባን ይሆናል፤ ለጌታ የማንሣት ቁርባን ይሆናል።
ቀኖቹንም በፈጸሙ ጊዜ በስምንተኛው ቀንና ከዚያም በኋላ፥ ካህናቱ የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና የሰላም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ውኃም ካለበት ከእስራኤል ማሰማርያ ከመንጋው ከሁለት መቶ አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ፤ ይህ እንዲያስተሰርይላችሁ እህል ቁርባን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለሰላም መሥዋዕት ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበሬ መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በጌታ ፊት እንዲሠምርለት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
በዚህም የእስራኤል ልጆች በሜዳ የሚያርዱትን መሥዋዕታቸውን እንዲያመጡ፥ ወደ ጌታ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ አምጥተዋቸው የአንድነት መሥዋዕት አድርገው ለጌታ እነርሱን እንዲያርዱ ለማድረግ ነው።
ስለ ሕዝቡ የአንድነት መሥዋዕት የሚቀርበውን በሬውንና አውራውን በግ አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ በመሠዊያውም ላይ በዙሪያው ረጨው፤
ለአንድነትም መሥዋዕት በሬንና አውራን በግ፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቁርባን በጌታ ፊት ለመሠዋት ውሰዱ፥ ዛሬ ጌታ ተገልጦላችኋልና።’ ”
የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቁርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለአንድነት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም።
“በመንጋው ውስጥ ተባዕት እያለው ለጌታ ተስሎት እያለ ነውር ያለበትን የሚሠዋ ተንኮለኛ ሰው የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “ስሜም በሕዝቦች መካከል የተፈራ ነውና።”
“የታወረውን ለመሥዋዕት ስታቀርቡ፥ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ይህንን ለገዢህ አቅርብ፤ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህንስ ይቀበላልን?” ይላል የሠራዊት ጌታ።
ቁርባኑንም ለጌታ ያቅርብ፤ ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለባትን የአንድ ዓመት እንስት ጠቦት ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለበትን አውራ በግ ለአንድነት መሥዋዕት፥
ለአንድነትም መሥዋዕት ሁለት በሬዎች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የአሚናዳብ ልጅ የነአሶን መባ ይህ ነበረ።
ለአንድነትም መሥዋዕት ሁለት በሬዎች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የፍዳሱር ልጅ የገማልኤል መባ ይህ ነበረ።
የሚቃጠል መሥዋዕትህን፥ ሥጋውንም ደሙንም በጌታ አምላክህ መሠዊያ ላይ አቅርብ። የመሥዋዕትህ ደም በጌታ አምላክህ መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ።
እናንተም ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን። ኅብረታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ ወደ ቤቴል ወጡ፤ እዚያም እያለቀሱ በጌታ ፊት ተቀመጡ፤ በዚያን ቀን እስኪመሽ ድረስ ጾሙ፤ በጌታ ፊት የሚቃጠል መሥዋትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ።