ሕዝቅኤል 43:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 ቀኖቹንም በፈጸሙ ጊዜ በስምንተኛው ቀንና ከዚያም በኋላ፥ ካህናቱ የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና የሰላም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 እነዚህ ቀኖች ካለፉ በኋላም፣ ከስምንተኛው ቀን ጀምሮ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የኅብረት መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያቀርባሉ። ከዚያም እኔ እቀበላችኋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 እነዚህ ቀኖች ካለፉ በኋላ ከስምንተኛው ቀን ጀምሮ ካህናቱ የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕታችሁን ያቀርባሉ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤” ይላል ልዑል እግዚአብሔር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ቀኖቹንም በፈጸሙ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ከዚያም በኋላ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ የደኅንነት መሥዋዕታችሁንም በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 ቀኖቹንም በፈጸሙ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ከዚያም በኋላ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን የደኅንነትንም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítulo |