ኢዮብ 6:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ሽብሮች በኔ ላይ ተሰልፈዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉን ቻይ አምላክ ፍላጻ በውስጤ ነው፤ መንፈሴም መርዙን ትጠጣለች፤ የእግዚአብሔር ማስደንገጥ ተሰልፎብኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉን የሚችል አምላክ በፍላጻዎቹ ወግቶኛል፤ መርዛቸውም በሰውነቴ ተሠራጭቶአል፤ የሚያስደነግጥ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ዙሪያዬን ከቦኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የእግዚአብሔር ፍላጻ በሥጋዬ ላይ ነው፤ መርዙም ደሜን ይመጥጣል። ለመናገር ስጀምርም ይወጋኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ድንጋጤ በላዬ ተሰልፎአል። |
ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ።
በዘጠኝም ሰዓት ኢየሱስ፥ “ኤሎሄ፥ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም “አምላኬ፥ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው።
እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን፥ ሰዎችን ለማስረዳት እንጥራለን፤ ስለ ራሳችን ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጥን ነን፤ ለእናንተም ሕሊና የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።