ኢዮብ 36:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብልጽግናህና ኃይልህ በሙሉ ከችግር የሚጠብቅህ ይመስልሃልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣ ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብትህና ሥልጣንህ ምንም ያህል ከፍተኞች ቢሆኑ፥ ከጭንቀት አያድኑህም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጭንቀት ካሉ ከችግረኞች ልመና የተነሣ አእምሮህ በፈቃድ አያስትህ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባለጠግነትህ የኃይልህም ብርታት ሁሉ ያለ ችግር እንድትሆን ሊረዳህ ይችላልን? |
በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።
ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፤ ዝገቱም በእናንተ ላይ ይመሰክራል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል፤ ለመጨረሻው ዘመን ሀብትን አከማችታችኋል።