ኢዮብ፦ እኔ ንጹሕ ነኝ፥ እግዚአብሔር ግን ፍርድ ከለከለኝ፥
“ኢዮብ እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ እግዚአብሔር ግን ፍትሕ ነሣኝ፤
ኢዮብ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ እግዚአብሔር ግን ፍትሕ ነፈገኝ።
ኢዮብ እንዲህ ብሎአልና፦ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ እግዚአብሔር ግን ፍርዴን አስወገደ፤
ኢዮብ፦ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ እግዚአብሔር ግን ፍርዴን አስወገደ፥
ከዚህም በላይ በደለኛ እንዳልሆንሁ፥ ከእጅህም የሚያድን እንደሌለ አንተ ታውቃለህ።
አንተ፦ ትምህርቴ የተጣራ ነው፥ በዓይንህም ፊት ንጹሕ ነኝ ትላለህ።
እነሆ፥ ሙግቴን አዘጋጅቻለሁ። ጽድቄም እንደሚገለጽ አውቃለሁ።
ነገር ግን በእጄ ዓመጽ የለም፥ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።”
እነሆ፥ ስለ ተደረገብኝ ግፍ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፥ ድረሱልኝ ብዬ ብጣራ ፍርድ የለኝም።
“ፍርዴን ያስቀረ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም ያስመረራት ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን!
ጽድቅን ለበስሁ እርሷም ለበሰችኝ፥ ፍርዴም እንደ ካባና እንደ ቆብ ነበረ።
ኢዮብም ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና እነዚያ ሦስቱ ሰዎች መመለስን ተዉ።
‘እኔ ንጹሕ ነኝ፥ በደል የለብኝም፤ ያለ እንከን ነኝ፥ ኃጢአትም የለብኝም፥
ፍትሕን እንምረጥ፥ መልካሙንም ነገር በመካከላችን እንወቅ።
እባካችሁ፥ ተመለሱ፥ በደል አይሁን፥ ጽድቄ በዚህ ነገር ነውና አንድ ጊዜ ተመለሱ።
በውኑ እግዚአብሔር ፍርድን ያጣምማልን? ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?
በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ ቁስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል።
ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤል ሆይ፦ “መንገዴ ከጌታ ተሰውራለች፥ ፍርዴም በአምላኬ ቸል ተብላለች” ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?