ኢዮብ 33:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ፦ ‘በፍጹም ለቃሌ መልስ አይሰጥም’ ብለህ፥ ስለምን ከእርሱ ጋር ትከራከራለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰውን አቤቱታ እንደማይሰማ፣ ለምን ታማርርበታለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ ‘እግዚአብሔር የሰውን አቤቱታ አይሰማም’ በማለት ለምን በእግዚአብሔር ላይ ታማርራለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ፦ ‘ቃሌን ሁሉ ለምን አይሰማኝም?’ ትላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ፦ ለቃሌ ሁሉ አይመልስልኝም ብለህ፥ ስለ ምን ከእርሱ ጋር ትከራከራለህ? |
ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?
ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?