Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 33:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እነሆ፥ አንተ በዚህ አቋምህ ትክክል አይደለህም፥ ‘እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣል’ ብዬ እመልስልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ነገር ግን እግዚአብሔር ከሰው ስለሚበልጥ፣ ትክክል እንዳልሆንህ እነግርሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “ኢዮብ ሆይ! ይህ ንግግርህ ስሕተት መሆኑን ልገልጥልህ እወዳለሁ፤ እግዚአብሔር ከሰው ሁሉ ይበልጣል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እነሆ፥ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ቃሌ​ንም አይ​ሰ​ማ​ኝም እን​ዴት ትላ​ለህ? ከሟች ሰው በላይ ያለ እርሱ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እነሆ፥ አንተ በዚህ ጻድቅ አይደለህም፥ እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣል ብዬ እመልስልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 33:12
20 Referencias Cruzadas  

እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ ቀና አይደለም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ ስሙ፥ በውኑ መንገዴ ቀና አይደለምን? ቀና ያልሆነውስ የእናንተ መንገድ አይደለምን?


እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፥ እርሱም በጥበባዊ ኃይሉም ጽኑ ነው።


“የእስራኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አልችልምን? ይላል ጌታ፤ እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ የእስራኤል ቤት ሆይ! እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ አላችሁ።


በምድር ላይ መልካምን የሚሠራ፥ ምንም ኃጢአት የማያደርግ ጻድቅ አይገኝምና።


“በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን የሚችል አምላክን መተቸት ይችላልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”


እኔ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉትም ባልንጀሮችህ እመልሳለሁ።


“ይህ ትክክል ነው ብለህ ታስባለህን? ወይስ፦ በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ ትላለህን?


ሰው ወደ እግዚአብሔር ለፍርድ ለመቅረብ ቀጠሮ አይሰጠውም።


እኔ ደግሞ ፈንታዬን እመልሳለሁ፥ እውቀቴንም እገልጣለሁ፥


እነሆ፥ እነኚህ የሥራዎቹ ጫፎች ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ማን ማስተዋል ይችላል?”


ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ እርሱንስ ተዳፍሮ በደኅና የቆየ ማን ነው?


በዚህ ሁሉ ኢዮብ አልበደለም፥ እግዚአብሔርንም አላማረረም።


“የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ሁሉን የሚችል አምላክን ፍጻሜ ልትመረምር ትችላለህን?


የጥበቡን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ማስተዋሉ እጥፍ ነውና። እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ።”


ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፥ ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios