ሕዝቅኤል 22:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ከአንቺ ጋር በምነጋገርበት ጊዜ ልብሽ መቋቋም ይችላልን? እጆችሽስ ይጸናሉን? እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፥ አደርገዋለሁም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እኔ ልቀጣሽ በምነሣበት ጊዜ፣ በልበ ሙሉነት መቆም ትችያለሽን? ወይስ እጅሽ ሊበረታ ይችላልን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ አደርገዋለሁም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እኔ እናንተን በምቀጣበት ጊዜ ወኔ የሚቀርላችሁ ይመስላችኋልን? ወይስ ለመከላከል ኀይል የሚኖራችሁ ይመስላችኋልን? እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ የተናገርኩትንም ቃል እፈጽማለሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እኔ በማደርግብሽ ወራት ልብሽ ይታገሣልን? ወይስ እጆችሽ ይጸናሉን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ አደርገውማለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 በውኑ እኔ በማደርግብሽ ወራት ልብሽ ይታገሣልን? ወይስ እጅሽ ትጸናለችን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ አደርገውማለሁ። Ver Capítulo |