ኢዮብ 21:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ እኔ ተመልከቱ፥ ተደነቁም፥ እጃችሁንም በአፋችሁ ላይ አኑሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተመልከቱኝና ተገረሙ፤ አፋችሁን በእጃችሁ ለጕሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስቲ ወደ እኔ ተመልከቱ፤ መናገር እስኪያቅታችሁ ድረስ ሁኔታዬ ያሠቅቃችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እኔ ተመልከቱ፥ ተደነቁም፤ እጃችሁንም በጕንጫችሁ ላይ አኑሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እኔ ተመልከቱ፥ ተደነቁም፥ እጃችሁንም በአፋችሁ ላይ አኑሩ። |
ከሩቅም ሆነው ዓይናቸውን ባነሡ ጊዜ አላወቁትም፤ ድምፃቸውንም አሰምተው አለቀሱ፥ እያንዳንዳቸውም መጐናጸፊያቸውን ቀደዱ፥ ወደ ላይም ወደ ራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
እነርሱም፥ “ዝም በል አንዲት ቃል እንዳትተነፍስ፤ ከእኛ ጋር ሁን፤ አባትም ካህንም ሁነን፤ ለአንተስ የአንድ ቤተሰብ ካህን ከመሆን ይልቅ በእስራኤል የአንዱ ነገድና ጐሣ ካህን ሆነህ ማገልገሉ አይሻልህምን?” አሉት።