Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 40:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 “እነሆ፥ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ፥ የምመልስልህ ምንድነው? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “እኔ ከንቱ ሰው፣ ምን እመልስልሃለሁ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “ጌታ ሆይ! እኔ ለምንም የማልጠቅም ከንቱ ሰው ነኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አፌን በእጄ ይዤ ዝም ከማለት በስተቀር፥ ለአንተ የምሰጠው መልስ የለኝም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 “አንተ ስታ​ስ​ተ​ም​ረኝ እኔ የም​መ​ል​ሰው ምን አለኝ? ይህ​ንስ እየ​ሰ​ማሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እከ​ራ​ከር ዘንድ እኔ ምን​ድን ነኝ? እጄን በአፌ ላይ ከማ​ኖር በቀር የም​መ​ል​ሰው ምን​ድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እነሆ፥ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ፥ የምመልስልህ ምንድር ነው? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 40:4
35 Referencias Cruzadas  

ከፍ ከፍ በማለት የተሞኝህ እንደሆነ፥ ክፉም ያሰብህ እንደሆነ፥ እጅህን በአፍህ ላይ ጫን።


መኮንኖች ከመናገር ዝም ይሉ፥ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር።


ወደ እኔ ተመልከቱ፥ ተደነቁም፥ እጃችሁንም በአፋችሁ ላይ አኑሩ።


ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፥ በአፈርና በአመድ ላይ ተቀምጬ እጸጸታለሁ።”


ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳን አልፈለገም፤ ነገር ግን ‘አምላክ ሆይ! እኔን ኀጢአተኛውን ማረኝ፤’ እያለ ደረቱን ይመታ ነበር።


እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።


እንዲህም አልሁ፦ “አምላኬ ሆይ፥ አፍሬአለሁ፤ አምላኬ ሆይ፥ ፊቴንም ወደ አንተ ለማንሣት እፈራለሁ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ከፍ ብሏልና፥ በደላችንም ወደ ሰማያት ወጥቷልና።


እነርሱም፥ “ዝም በል አንዲት ቃል እንዳትተነፍስ፤ ከእኛ ጋር ሁን፤ አባትም ካህንም ሁነን፤ ለአንተስ የአንድ ቤተሰብ ካህን ከመሆን ይልቅ በእስራኤል የአንዱ ነገድና ጐሣ ካህን ሆነህ ማገልገሉ አይሻልህምን?” አሉት።


ለባርያህ ካሳየኸው ከጽኑ ፍቅርና ከታማኝነትህ ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፥ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበር፥ አሁን ግን ለሁለት ወገን የተከፈልኩ ሆንሁ።


አብርሃምም መለሰ ዓለም፦ “እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፥


“ኀጢአተኞችን ለማዳን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ፤” የሚለው ቃል የታመነና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋነኛው እኔ ነኝ፤


ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ፊት ወድቆ፦ “ጌታ ሆይ! እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከኔ ራቅ፤” አለው።


እነሆ፥ እጄን በላያቸው ላይ አነሣለሁ፥ በምርኮ ተገዝተውላቸው ለነበሩት ራሳቸው በምርኮ ይዘረፋሉ፤ የሠራዊት ጌታም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


ጌታ ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድሪቷ ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።


አሕዛብ ያያሉ፥ በኀይላቸው ሁሉ ያፍራሉ፤ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮዎቻቸውም ይደነቁራሉ።


ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።


እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ ጌታም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።


ከመተላለፌ ሁሉ አድነኝ፥ የሞኞች መሳለቂያ አታድርገኝ።


የእርምጃዬን ቍጥር አስታውቀው፥ እንደ መስፍንም ሆኜ እቀርብለት ነበር።”


የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመምዋገት ምነው በቻለ!


በደረሰብንም ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፥ አንተ እውነት አድርገሃልና፥ እኛም ኃጢአት አድርገናል።


የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ እንደ ዛሬው እኛ አምልጠን ቀርተናል፥ እነሆ በፊትህ በበደላችን አለን፥ በዚህ ምክንያት በፊትህ ሊቆም የሚችል የለም።


ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጉዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “ጌታ ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።


ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ።


ኢዮብም መለሰ፤ እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦


ተስፋ የሆነው እንደሆነ አፉን በአፈር ውስጥ ያኑር።


ለምጹም በቆዳው ላይ ሰፍቶ ቢወጣ፥ ካህኑ ማየት እስከሚችልበት አካል የለምጹ ደዌ የታመመውን ሰው ቆዳ ሁሉ ከራሱ እስከ እግሮቹ ድረስ ቢሸፍነው፥


እኛ ከጨለማ የተነሣ በሥርዓት መናገር አንችልምና ለርሱ የምንለውን አስታውቀን።


ያደረግሽውን ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ እንድታስቢውና እንድታፍሪ፥ ከውርደትሽም የተነሣ ደግሞ አፍሽን እንዳትከፍቺ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios