ኤርምያስ 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሐሰትን ለመናገር፣ ምላሳቸውን እንደ ቀስት ገተሩ፤ በእውነት ሳይሆን፣ በሐሰት በምድሪቱ ገነኑ፤ ከክፋት ወደ ክፋት ሄዱ፤ እኔንም አላወቁኝም፤” ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ በአንደበታቸው ሐሰት ለመናገር ዘወትር የተዘጋጁ ናቸው፤ ስለዚህም በምድሪቱ ላይ በእውነት ፈንታ ሐሰት ነግሦአል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ከአንዱ ኃጢአት ወደ ሌላው ኃጢአት ይተላለፋሉ፤ የእኔንም አምላክነት ዐውቀው አላከበሩኝም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምላሳቸውን ለሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፥ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፥ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና እኔንም አላወቁምና፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።
እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ ‘ጌታን እወቅ’ ብሎ ከእንግዲህ ወዲህ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል ጌታ። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስምና።”
“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”
ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እነርሱንም አናግራቸዋለሁ፤ የጌታን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና” አልሁ። እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፥ እስራቱንም ቈርጠዋል።
በዚህ ዘማዊና ኀጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅም በአባቱ ግርማ፥ ከቅዱሳን መላእክት ጋር ሲመጣ ያፍርበታል።”
በምንም ዓይነት ነገር በተቃዋሚዎቻችሁ አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፤ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤
ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅዱሳን ሁሉ ስለ ተሰጠው እምነት እንድትጋደሉ እንድመክራችሁና እንድጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።
ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የእንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች።