ኤርምያስ 44:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ መዓቴና ቁጣዬ ወረዱ፥ በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ነደዱ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ፈረሱ ባድማም ሆኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ መዓቴና ቍጣዬ ፈሰሰ፤ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ነደደ፤ ዛሬ እንደሚታዩትም ማንም የማይኖርባቸው ፍርስራሾች አደረጋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ቊጣዬንና መዓቴን በማፍሰስ በእሳት እንዲጋዩ አደረግሁ፤ እነርሱም ዛሬ እንደሚታዩት ሁሉ ፍርስራሾችና ባድማ ሆነዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ መዓቴና መቅሠፍቴ ወረደ፤ በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ነደደ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ጠፍና ባድማ ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ መዓቴና ቍጣዬ ፈሰሱ፥ በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ነደዱ፥ ዛሬም እንደ ሆነው ፈረሱ ባድማም ሆኑ። |
እኔም፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት፤ እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና፤ የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፤ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና፤ ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤
የዳዊት ቤት ሆይ! ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፥ የተበዘበዘውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ።’
እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ ይላል ጌታ፥ ወደዚህችም ከተማ እመልሳቸዋለሁ፤ እርሷንም ይወጋሉ ይይዙአታልም በእሳትም ያቃጥሉአታል፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”
ጌታ በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቁጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በጌታ ፊት ይቀርብ ይሆናል፥ ሁሉም ከክፉ መንገዱ ይመለስ ይሆናል።”
እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ! ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለጌታ እራሳችሁን ግረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።”
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ተናግሮአልና፦ ቁጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ወረደ፥ እንዲሁ ወደ ግብጽ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይወርድባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለመሣቀቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ትሆናላችሁ፥ ይህንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩትም።
ጌታም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኩሰት መታገሥ አልቻለም፤ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ መሣቀቂያም መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደሆነ የሚኖርባት የለም።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቁጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይወርዳል፤ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።”
ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የሙሽራውን ድምፅና የሙሽራይቱን ድምፅ አጠፋለሁ።
አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ መካከል ታላቅ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፥ በአውራጆች መካከል ልዕልት የነበረች ተገዢ ሆናለች።
በርኩሰትሽ ሴሰኝነት አለ፥ መዓቴን በአንቺ ላይ እስክጨርስ ድረስ ከእንግዲህ ወዲያ ከርኩሰትሽ ንፁህ አትሆኚም ምክንያቱም አነጻሁሽ ነገር ግን ንፁህ አልሆንሺምና።
ንዴቴ ያልፋል፥ ቁጣዬም በእነርሱ ላይ እንዲያርፍ አደርጋለሁ፥ እጽናናለሁም፥ ቁጣዬን በእነርሱ ላይ በፈጸምሁ ጊዜ እኔ ጌታ በቅንዓቴ እንደ ተናገርሁ ያውቃሉ።
በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፥ በቅርብ ያለውም በሰይፍ ይወድቃል፥ በሕይወት የተረፈውና የዳነውም በራብ ይሞታል፥ መዓቴን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።
ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።
በማያውቋቸው በባዕዳን አሕዛብ መካከል በዐውሎ ነፋስ በተንኳቸው። ስለዚህ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚዘዋወርባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፤ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።