Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 51:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ በየአደባባዩ ራስ ላይ ተኝተዋል፤ በጌታ ቁጣና በአምላክሽ ተግሣጽ ተሞልተዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ወንዶች ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ፣ በየጐዳናው አደባባይ ላይ ተኝተዋል። የእግዚአብሔር ቍጣ፣ የአምላክሽም ተግሣጽ ሞልቶባቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ልጆችሽ በወጥመድ ውስጥ እንደ ተያዘ ድኩላ በየመንገዱ አደባባይ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፤ በእነርሱም ላይ የአምላክሽ የእግዚአብሔር ተግሣጽና ቊጣ ወርዶባቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ልጆ​ችሽ ዝለ​ዋል፤ እንደ ጠወ​ለገ ቅጠ​ልም በየ​መ​ን​ገዱ ዳር ወድ​ቀ​ዋል፤ በአ​ም​ላ​ክሽ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣና ተግ​ሣጽ ተሞ​ል​ተ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ልጆችሽ ዝለዋል፥ በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ በአደባባይ ሁሉ ራስ ላይ ተኝተዋል፥ በእግዚአብሔር ቍጣና በአምላክሽ ተግሣጽ ተሞልተዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 51:20
27 Referencias Cruzadas  

ተደነቁ ደንግጡም፤ ጨፍኑ ታወሩም! ስክሩም፥ በወይን ጠጅ አይደለም፤ ተንገዳገዱ፥ በመጠጥ አይደለም።


ብላቴኖች ይደክማሉ፥ ይታክታሉም፤ ጐበዛትም ፈጽሞ ይወድቃሉ።


አስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን አስበላቸዋለሁ፥ እንደ ጣፋጭም ወይን ጠጅ ደማቸውን ጠጥተው ይሠክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ ጌታ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብ ኃያል እንደሆንሁ ያውቃል።


የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነዶአል፤ እጁን አንሥቶ መቶአቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ቁጣው ገና አልተመለሰም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።


ከጌታ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ! ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል ጨልጠሽውማል።


ስለዚህ ያለ ወይን ጠጅ የሰከርሽ አንቺ ችግረኛ፥ ይህን ስሚ፤


እነሆ፥ ጌታ መዓቱን በቁጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።


ተጨንቀውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ክፉኛ ሲራቡም ይቈጣሉ፤ ወደ ላይ እየተመለከቱ ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይራገማሉ።


ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይጣላሉ፤እነርሱንና ሚስቶቻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም፤ ክፋታቸውንም በእነርሱ ላይ አወርድባቸዋለሁ።


ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ ደዌ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቁት አገር ሄደዋልና።’”


ሳምኬት። ጌታ ኃያላኖቼን ሁሉ ከውስጤ አስወገዳቸው፥ ጐልማሶቼን ያደቅቅ ዘንድ ጉባኤን ጠራብኝ፥ ጌታ ድንግሊቱን የይሁዳን ልጅ በመጥመቂያ እንደሚረገጥ አድርጎ ረገጣት።


ቆፍ። ውሽሞቼን ጠራሁ እነርሱም አታለሉኝ፥ ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ ሰውነታቸውን ያበረቱ ዘንድ መብል ሲፈልጉ በከተማ ውስጥ ሞቱ።


ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።


ካፍ። እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፥ ጽኑ ቁጣውን አፍስሶአል፥ እሳትን በጽዮን ውስጥ አቃጠለ፥ መሠረትዋንም በላች።


ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚመስሉ የከበሩ የጽዮን ልጆች፥ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እንዴት ተቈጠሩ!


ጉልማሶች ወፍጮን ተሸከሙ፥ ልጆችም ከእንጨት በታች ተሰናከሉ።


መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፥ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል።


መረቤን በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ባቢሎንም አመጣዋለሁ፥ በዚያም በእኔ ላይ ለፈጸመው ክሕደት ከእርሱ ጋር እፋረዳለሁ።


እኔ በማዘጋጅላችሁ መሥዋዕት እስክትጠግቡ ድረስ ጮማ ትበላላችሁ፥ እስክትሰክሩም ድረስ ደም ትጠጣላችሁ።


አጋዘን ሚዳቋ፥ ቦራይሌ፥ የሜዳ ፍየል፥ ዋላ፥ ድኩላንና ብሖር፤


“እርሱን በመተው ክፉ ድርጊት ከመፈጸምህ የተነሣ፥ እስክትደመሰስ ፈጥነህም እስክትጠፋ ድረስ እጅህ በነካው ሁሉ ላይ ጌታ ርግማንን፥ ሁከትንና መደናገርን ይልክብሃል።


እርሱ ደግሞ በቁጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር የቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos