ኤርምያስ 25:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ አደርጋታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገር ግን ሰባው ዓመት ከተፈጸመ በኋላ፣ የባቢሎንን ንጉሥና ሕዝቡን፣ የባቢሎናውያንንም ምድር ስለ በደላቸው እቀጣቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለዘላለምም ባድማ አደርጋታለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሰባው ዓመት ሲፈጸም ባቢሎንን፥ ሕዝብዋንና ንጉሥዋን በበደላቸው ምክንያት እቀጣቸዋለሁ፤ የባቢሎንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ ሆና እንድትቀር አደርጋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም አጠፋቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘላለም ባድማ አደርጋታለሁ። |
በኤርምያስም አንደበት የተነገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ ነገረ፥ ደግሞም በጽሑፍ እንዲህ ብሎ አወጀ፦
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸዋልም አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ ስለ ክፉ ሥራችሁ እጐበኛችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።
ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፥ እስከምጐበኛቸውም ቀን ድረስ በዚያ ይቆያሉ፥ ይላል ጌታ፤ ከዚያም በኋላ አውጥቼአቸው ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ።”
በራሱ ምድር ላይ መውደቅያው እስከሚመጣ ጊዜ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁም ለልጅ ልጁም ያገለግላሉ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን አገልጋይ ያደርጉታል።
“ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህችም ስፍራ እናንተን በመመለስ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።