Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 29:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህችም ስፍራ እናንተን በመመለስ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰባው ዓመት የባቢሎን ቈይታችሁ በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ ልመልሳችሁ የገባሁላችሁን መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በባቢሎን የምትኖሩበት ሰባው ዓመት ከተፈጸመ በኋላ እንደገና እናንተን በምሕረት እጐበኛለሁ፤ ወደ አገራችሁ እንድመልሳችሁ የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈጽማለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰባው ዓመት በባ​ቢ​ሎን በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ እጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ለሁ፥ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እመ​ል​ሳ​ችሁ ዘንድ መል​ካ​ሚ​ቱን ቃሌን እፈ​ጽ​ም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 29:10
22 Referencias Cruzadas  

በኤርምያስ አንደበት የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አደረገች።


በኤርምያስም አንደበት የተነገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ ነገረ፥ ደግሞም በጽሑፍ እንዲህ ብሎ አወጀ፦


በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት፥ በኤርምያስ አፍ የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፥ ይህም በመንግሥቱ ሁሉ በአዋጅና በጽሑፍ እንዲያስነግር ነው፤


የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ “የሰማያት አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፥ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል፤


አንተ ተነሥ ለጽዮንም ራራ፥ የጸጋዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና፥


ይህችም ምድር ሁሉ ባድማና መሣቀቂያ ትሆናለች፤ እነዚህም አሕዛብ ለባቢሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ያገለግላሉ።


ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ አደርጋታለሁ።


ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፥ እስከምጐበኛቸውም ቀን ድረስ በዚያ ይቆያሉ፥ ይላል ጌታ፤ ከዚያም በኋላ አውጥቼአቸው ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ።”


በራሱ ምድር ላይ መውደቅያው እስከሚመጣ ጊዜ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁም ለልጅ ልጁም ያገለግላሉ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን አገልጋይ ያደርጉታል።


እርሱ፦ “ለረጅም ጊዜ በምርኮ ስለምትቆዩ ቤቶችን ሠርታችሁ ተቀመጡ፥ አታክልትንም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ” ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢሎን ልኮአልና።’ ”


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ኔሔላማዊውን ሸማያንና ዘሩን እቀጣለሁ፤ በጌታ ላይ ዓመፅን ተነናግሯአልና ከእርሱ ዘር በዚህ ሕዝብ መካከል ተቀምጦ፥ እኔ ለሕዝቤ የማደርገውን መልካም ነገር የሚያይ ማንም አይኖርም፥ ይላል ጌታ።’ ”


እነሆ፥ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስበት ዘመን ይመጣልና፥ ይላል ጌታ፤ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ እነርሱም ይወርሱአታል፥ ይላል ጌታ።”


“እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።


ስለዚህ እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከሕዝቦች መካከል እሰበስባችኋለሁ፥ ከተበተናችሁባቸው አገሮችም እሰበስባችኋለሁ፥ የእስራኤልንም ምድር ለእናንተ እሰጣችኋለሁ።


የባሕሩም ዳር ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሆናል፥ በዚያም ይሰማራሉ፤ በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ ማታ ይተኛሉ፤ ጌታ አምላካቸው ይጐበኛቸዋልና፥ ምርኮአቸውንም ይመልሳል።


የጌታም መልአክ መልሶ፦ “አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ፥ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን የኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?” አለ።


ለምድሩ ሕዝብና ለካህናት ለሁሉም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ስታለቅሱ፥ በውኑ ለእኔ ነው የጾማችሁልኝ?


እርሷም በሞዓብ ምድር ሳለች ጌታም ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እህልም እንደሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos