ኢሳይያስ 46:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ቤል ተዋረደ፥ ናባው ተሰባበረ፤ ጣዖቶቻቸው በእንስሳና በከብት ላይ ተጭነዋል፤ ሸክሞቻችሁ ለደካማ እንስሳ ከባድ ጭነት ሆነዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ቤል ተዋረደ፤ ናባው እጅግ ዝቅ አለ፤ ጣዖቶቻቸው በአጋሰስ ተጭነዋል፤ ይዘዋቸው የሚዞሩት ምስሎች ሸክም ናቸው፤ ለደከሙ እንስሳት ከባድ ጭነት ናቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 “ቤልና ኔቦ የተባሉት የሐሰት አማልክት ያጐነብሳሉ፤ ጣዖቶቻቸው በጭነት እንስሶች ላይ ተጭነዋል፤ የተጫኑት ምስሎች ለደካማ እንስሳ ከባዶች ናቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ቤል ወደቀ፤ ዳጎን ተሰባበረ፤ ምስሎቻቸውም እንደ ትቢያ ሆኑ፤ አራዊትና እንስሳም ይረግጡአቸዋል፤ እንደ ፋንድያም ሸክም የሚያጸይፉ ናቸውና አያነሡአቸውም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ቤል ተዋረደ፥ ናባው ተሰባበረ፥ ጣዖቶቻቸው በእንስሳና በከብት ላይ ተጭነዋል፥ ሸክሞቻችሁ ለደካማ እንስሳ ከባድ ጭነት ሆነዋል። Ver Capítulo |