Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 25:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህም በኋላ ሰባው ዓመት ሲፈጸም ባቢሎንን፥ ሕዝብዋንና ንጉሥዋን በበደላቸው ምክንያት እቀጣቸዋለሁ፤ የባቢሎንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ ሆና እንድትቀር አደርጋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ነገር ግን ሰባው ዓመት ከተፈጸመ በኋላ፣ የባቢሎንን ንጉሥና ሕዝቡን፣ የባቢሎናውያንንም ምድር ስለ በደላቸው እቀጣቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለዘላለምም ባድማ አደርጋታለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ አደርጋታለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “ሰባው ዓመ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉ​ሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ምድር ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘላለም ባድማ አደርጋታለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 25:12
26 Referencias Cruzadas  

በነገሠም በመጀመሪያው ዓመት እኔ ዳንኤል ቅዱሳት መጻሕፍትን እየተመለከትኩ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለኤርምያስ በነገረው መሠረት ኢየሩሳሌም ፍርስራሽ ሆና የምትቈይባት ዘመን ሰባ ዓመት መሆኑን ዐወቅሁ።


የባቢሎን መንግሥት ከመንግሥታት ሁሉ እጅግ የተዋበች ናት፤ ለሕዝብዋም መመኪያ ናት፤ ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር ባቢሎንን እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ እገለብጣታለሁ!


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በባቢሎን የምትኖሩበት ሰባው ዓመት ከተፈጸመ በኋላ እንደገና እናንተን በምሕረት እጐበኛለሁ፤ ወደ አገራችሁ እንድመልሳችሁ የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈጽማለሁ፤


ባቢሎንን ረግረግ ስለማደርጋት የአልቅት መፈልፈያ ትሆናለች፤ ባቢሎንን ሁሉን ነገር ጠራርጎ በሚወስድ መጥረጊያ እጠርጋታለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”


እኔ ለዘለዓለሙ ምድራችሁን ባድማ አደርጋለሁ፤ ዳግመኛም በከተሞቻችሁ የሚኖር አይገኝም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ።


ባቢሎናውያን ስላደረጉትም ክፋት ሁሉ ቅጣታቸውን እንዲያገኙ አደርጋለሁ፤ ብዙ ሕዝቦችና ታላላቅ ነገሥታት ባሪያ አድርገው ይገዙአቸዋል።’ ”


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሕዝቡ ጠባቂዎች መሆን ስለሚገባቸው መሪዎች እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን እንደሚገባ አልጠበቃችሁም፤ ይልቁንም አሳዳችሁ በተናችሁ፤ ስለዚህ ስለ ፈጸማችሁት ክፋት ሁሉ እቀጣችኋለሁ።


“ቤልና ኔቦ የተባሉት የሐሰት አማልክት ያጐነብሳሉ፤ ጣዖቶቻቸው በጭነት እንስሶች ላይ ተጭነዋል፤ የተጫኑት ምስሎች ለደካማ እንስሳ ከባዶች ናቸው።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት በሆነው በሣርጎን ትእዛዝ የአሦራውያን ጦር አዛዥ የፍልስጥኤማውያን ከተማ በሆነችው በአሽዶድ ላይ አደጋ ጣለ፤


የኒምሪም ወንዞች ደርቀዋል፤ ምንም ልምላሜ ሳይቀር በአጠገቡ ያለው ሣር ደርቆአል።


ኢዮአቄም በነገሠ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይሁዳን ወረረ፤ ኢዮአቄምም ሦስት ዓመት ከገበረለት በኋላ እንደገና ዐመፀ፤


እግዚአብሔር በነቢዩ ኤርምያስ አማካይነት አስቀድሞ የተናገረው የትንቢት ቃል፥ ቂሮስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በመጀመሪያው ዓመት ተፈጸመ፤ ከዚህ የሚከተለውን ዐዋጅ እንዲያወጣና በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ሁሉ በጽሑፍ በማስተላለፍ ከፍ ባለ ድምፅ ለሕዝቡ በንባብ እንዲገለጥ ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር ቂሮስን አነሣሣው።


ባቢሎን ሆይ! አፍራሽዋ ባቢሎን! በእኛ ላይ ያደረግሽብንን የክፋት ብድራት ሁሉ በአንቺ ላይ የሚመልስብሽ የተባረከ ነው።


አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል።


ሕዝቦች ሁሉ ያገለግሉታል፤ እንዲሁም የገዛ ሕዝቡ የሚወድቅበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ ለልጁና ለልጅ ልጁ ጭምር ተገዢዎች ይሆናሉ፤ ከዚያም በኋላ የእርሱ ሕዝብ ለኀያላን ሕዝቦችና ለታላላቅ ነገሥታት አገልጋዮች ይሆናሉ።’


ሐሳቤን ወደ እነርሱ እስከምመልስበት ጊዜ ድረስ፥ እነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ወደ ባቢሎን ተወስደው በዚያ ይኖራሉ። ከዚያም በኋላ እንደገና መልሼ ወደዚህ ስፍራ አመጣቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ታዲያ እርሱ መረቡን እያራገፈና ያለምሕረት ሕዝቦችን እየፈጀ መቀጠል አለበትን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios