ኢሳይያስ 9:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጡቦቹ ወድቀዋል፤ እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤ የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤ እኛ ግን በዝግባ እንተካለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ በሙሉ፣ ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች ይህን ያውቃሉ፤ በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብና በሰማርያ ከተማም የሚኖሩ ሁሉ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር መሆኑን ያውቃሉ፤ ሆኖም፥ ትዕቢተኞችና እልኸኞች ሆነው እንዲህ ይላሉ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤፍሬም ሕዝብ ሁሉና በሰማርያ የሚኖሩ ያውቃሉ፤ በትዕቢትና በልብ ኵራትም እንዲህ ይላሉ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በትዕቢትና በልብ ኵራት፦ ጡቡ ወድቆአል፥ ነገር ግን በተወቀረ ድንጋይ እንሰራለን፥ የሾላ ዛፎች ተቈርጠዋል፥ ነገር ግን ዝግባን እንተካባቸዋለን የሚሉ በኤፍሬምና በሰማርያ የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ ያውቃሉ። |
ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፥ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ፥ በለምለሙ ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮላት!
ለዳዊት ቤት፤ “ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል” የሚል ወሬ በደረሰ ጊዜ፤ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የአካዝና የሕዝቡ ልብ እንዲሁ ተናወጠ።
እነሆ፥ አፈር ደልድለው የመሸጉ፥ ከተማይቱን ሊይዙአት ቀርበዋል፤ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም የተነሣ ከተማይቱ ለሚዋጉአት ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች፤ የተናገርኸውም ሆኖአል፥ እነሆም፥ አንተ ታየዋለህ።
ንጉሡ ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝቦች እጆች ይንቀጠቀጣሉ፥ እንደ መንገዳቸው መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
ዓይኔም አይራራም፥ እኔም አላዝንም፥ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ የምቀሥፍም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፥ ቤተ መንግሥቶችን ሠርቶአል፤ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፤ እኔ ግን በእርሱ ከተሞች ላይ እሳት እልካለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ትበላለች።
ኤዶም፦ “እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን” ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ የክፋት አገር፥ ጌታ ለዘለዓለም የተቆጣው ሕዝብ ብለው ይጠሩአቸዋል።”
“እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ ሥርንና ቅርንጫፍንም አያስቀርላቸውም።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።