ሕዝቅኤል 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ዓይኔም አይራራም፥ እኔም አላዝንም፥ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ የምቀሥፍም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 በርኅራኄ ዐይን አልመለከትሽም፤ ምሕረት አላደርግልሽም፤ ስለ አካሄድሽና በመካከልሽ ስላለው ጸያፍ ተግባር፣ ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ፤ በዚያ ጊዜ፣ የምቀሥፍ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም፤ በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ዐይኔም አይራራም፤ እኔም ይቅር አልልም፤ መንገድሽንም አመጣብሻለሁ፤ ርኵሰትሽም በመካከልሽ ነው፤ እኔም እግዚአብሔር የምቀሥፍ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም፥ እንደ መንገድሽም መጠን አመጣብሻለሁ፥ ርኵሰትሽም በመካከልሽ ይሆናል፥ እኔም እግዚአብሔር የምቀሥፍ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። Ver Capítulo |