ኢሳይያስ 19:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው እርባና ቢስ ይሆናል። ፈርዖንን “እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን” እንዴት ትሉታላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጣኔዎስ አለቆች በጣም ቂሎች ናቸው፤ የፈርዖን ጠቢባን ምክራቸው የማይረባ ነው፤ ፈርዖንን፣ “እኔ ከጥበበኞች አንዱ ነኝ፤ የጥንት ነገሥታትም ደቀ መዝሙር ነኝ” እንዴት ትሉታላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጾዓን ያሉ የንጉሡ ባለ ሥልጣኖች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ጠቢባን የሆኑት የግብጽ ንጉሥ አማካሪዎች ጥቅም የሌለው ምክር ይመክራሉ፤ እንዴት አድርገው ለንጉሡ “እኛ ብልኆች ነን፤ ዘራችንም ከቀድሞ ነገሥታት ሲወርድ፥ ሲዋረድ የመጣ ነው” ይላሉ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ይሆናሉ፤ ነገሥታትን የሚመክሩ ጥበበኞችም ምክራቸው ስንፍና ትሆናለች። ንጉሥን፥ “እኛ የጥበበኞች ልጆች፥ የቀደሙ ነገሥታትም ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሰነፎች ናቸው፥ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው ድንቍርና ሆነች። ፈርዖንን እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ? |
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “እንቁራሪቶቹን ከእኔና ከሕዝቤ እንዲያርቅ ወደ ጌታ ጸልዩልኝ፤ ለጌታም እንዲሠዋ ሕዝቡን እለቅቃለሁ” አላቸው።
የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፥ ዕቅዳቸውንም መና አስቀራለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን፥ የሙታን መናፍስትን፥ መናፍስት ጠሪዎቻቸውንና የጠንቋዮቻቸውን ምክር ይጠይቃሉ።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ አስደማሚ ነገርን ተአምራትንም እንደገና አደርጋለሁ፤ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።
ሰው ሁሉ ቂላ ቂልና እውቀት የሌለው ሆኖአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።
ከአንተ ጋር ቃል የተገባቡ ሰዎች ሁሉ ወደ ዳርቻህ ሰደዱህ፥ የታመንሃቸው ሰዎች አታለሉህ፥ አሸነፉህም፥ በበታችህም ወጥመድ ዘረጉብህ፥ እነርሱም ማስተዋል የላቸውም።
በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብጽ ካለችው ከጣኔዎእ ከሰባት ዓመት በፊት የተቈረቈረች ከተማ ነበረች።