ኢሳይያስ 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የጣኔዎስ አለቆች ተሞኝተዋል፤ የሜምፎስም አለቆች ተታለዋል፤ የነገዶችዋ የማዕዘን ድንጋዮች የሆኑት ግብጽን አስተዋታል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 የጣኔዎስ አለቆች ተሞኝተዋል፤ የሜምፊስ ሹማምት ተታልለዋል፤ የሕዝቧ ዋና ዋናዎች፣ ግብጽን አስተዋታል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 የጾዓን ባለ ሥልጣኖች ሞኞች ሆኑ፤ የሜምፊስ መሪዎችም ተታለሉ፤ የሕዝብዋ ከፍተኛ አማካሪዎች ግብጽን አሳትዋት። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የጣኔዎስ አለቆች አለቁ፤ የሜምፎስም አለቆች ከፍ ከፍ አሉ፤ ግብፃውያን በየወገናቸው ተሳሳቱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ሆነዋል፥ የሜምፎስም አለቆች ተሸንግለዋል፥ የነገዶችዋ የማዕዘን ድንጋዮች የሆኑ ግብጽን አሳቱ። Ver Capítulo |