ኢሳይያስ 13:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓለምን ስለ ክፋቷ፤ ክፉዎችንም ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የትዕቢተኞችን እብሪት እሽራለሁ፤ የጨካኞችንም ጉራ አዋርዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓለምን ስለ ክፋቷ፣ ክፉዎችንም ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የትዕቢተኞችን እብሪት እሽራለሁ፤ የጨካኞችንም ጕራ አዋርዳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዓለምን ስለ ክፋቱ፥ ክፉዎችን ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የኲራተኞችን ማን አለብኝነት አዋርዳለሁ፤ የትዕቢተኛውንም ጭካኔ አጠፋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዓለም ሁሉ ላይ ክፋትን አዝዛለሁ፤ የኀጢአተኞችንም ኀጢአት እጐበኛለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኵራት እሽራለሁ፤ የጨካኞቹንም ኵራት አዋርዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓለሙን ስለ ክፋታቸው ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ፥ የትዕቢተኞችንም ኵራት እሽራለሁ፥ የጨካኞቹንም ኵራት አዋርዳለሁ። |
ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
ይህም ነገር የሠራዊት ጌታ ይህንን በጆሮዬ ነገረኝ፤ እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቁጣውን ሊያመጣባቸው፥ እነሆ፥ ጌታ ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ያፈሰሰችውን ደም ትገልጣለች፥ የተገደሉትንም ከእንግዲህ ወዲህ አትሸሽግም።