Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 26:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቁጣውን ሊያመጣባቸው፥ እነሆ፥ ጌታ ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ያፈሰሰችውን ደም ትገልጣለች፥ የተገደሉትንም ከእንግዲህ ወዲህ አትሸሽግም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በምድር ላይ የሚኖረውን ሕዝብ ስለ ኀጢአቱ ለመቅጣት፣ እነሆ፤ እግዚአብሔር ከመኖሪያው ወጥቶ ይመጣል፤ ምድር በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤ የተገደሉትንም ከእንግዲህ አትሸሽግም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በምድር ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ስለ ኃጢአታቸው ለመቅጣት እግዚአብሔር ከሰማይ መኖሪያው ይገለጣል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ተሸሽገው የሚኖሩ የነፍሰ ገዳዮች ሥራ ይጋለጣል፤ ምድርም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ታጋልጣለች። የተገደሉትንም አትደብቅም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ ከመ​ቅ​ደሱ መቅ​ሠ​ፍ​ቱን ያመ​ጣል፤ ምድ​ርም ደም​ዋን ትገ​ል​ጣ​ለች፤ ሙታ​ኖ​ች​ዋ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ከ​ድ​ንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቍጣውን ያመጣባቸው ዘንድ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፥ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፥ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 26:21
28 Referencias Cruzadas  

ጌታ፥ “በፀሐይ ጮራ እንደ ደረቅ ትኩሳት፥ በአጨዳም ወራት እንደ ጠል ደመና ሆኜ በማደሪያዬ በጸጥታ ተቀምጬ እመለከታለሁ” ብሎኛል።


ዓለምን ስለ ክፋቷ፤ ክፉዎችንም ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የትዕቢተኞችን እብሪት እሽራለሁ፤ የጨካኞችንም ጉራ አዋርዳለሁ።


“ምድር ሆይ፥ ደሜን አትክደኚ፥ ለጩኸቴም ማረፊያ አይኑር።


የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤”


ስለዚህም ይህ ትውልድ ተጠያቂ የሚሆነው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በፈሰሰው በነቢያት ሁሉ ደም፥


እናንተ ሞኞች! የውጭውን የፈጠረ እርሱ የውስጡንስ ደግሞ አለፈጠረምን?


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ ከመቅደሴ ሊያርቁኝ፥ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚፈጽሙትን ታላቅ ርኩሰት ታያለህን? ደግሞም ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኩሰት ታያለህ።


በእርሷም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም፥ በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።


ሰማይ በደሉን ይገልጥበታል፥ ምድርም ትነሣበታለች።


በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?


ይህም ነገር የሠራዊት ጌታ ይህንን በጆሮዬ ነገረኝ፤ እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።


እነሆ፥ በፊቴ እንዲህ ተጽፎአል፦ “ዝም አልልም፤ ነገር ግን እንደ ሥራው እሰጠዋለሁ፤ የእጃቸውንም እከፍላቸዋለሁ።


በተራሮችም ላይ ስላጠኑ፥ በኮረብቶችም ላይ ስለ ሰደቡኝ፥ ስለዚህ አስቀድመው ለሠሩት ሥራቸውን የእጃቸውን እሰጣቸዋለሁ።”


የጩኸት ድምፅ ከከተማ፥ ድምፅም ከመቅደስ፥ በጠላቶቹ ላይ ፍዳን የሚያመጣ የጌታ ድምፅ ተሰምቶአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios