ሆሴዕ 7:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመሄድ ላይ ሳሉ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎች አወርዳቸዋለሁ፤ በጉባኤያቸው ላይ እንደተላለፈው እገሥጻቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲበርሩ፣ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም ጐትቼ አወርዳቸዋለሁ። ስለ ክፉ ሥራቸውም፣ በጉባኤ መካከል እቀጣቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚዘዋወሩበት ቦታ ሁሉ ወጥመዴን ዘርግቼ እንደ ወፍ እይዛቸዋለሁ፤ ስለ ሠሩትም ክፉ ሥራ እቀጣቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲሄዱም አሽክላዬን እዘረጋባቸዋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም አወርዳቸዋለሁ፤ መከራቸውን ሲሰሙ እገሥጻቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲሄዱ አሽክላዬን እዘረጋባቸዋለሁ፥ እንደ ሰማይ ወፎች አወርዳቸዋለሁ፥ መከራቸውን ሲሰሙ እገሥጻቸዋለሁ። |
ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።
“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ፥ ይላል ጌታ፥ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እልካለሁ፥ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድኑአቸዋል።
መረቤን በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ባቢሎንም አመጣዋለሁ፥ በዚያም በእኔ ላይ ለፈጸመው ክሕደት ከእርሱ ጋር እፋረዳለሁ።