ሕዝቅኤል 22:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሜተኞች ሰዎች ደምን ሊያፈስሱ በአንቺ ውስጥ ነበሩ፥ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፥ በመካከልሽ ሴሰኝነትን አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደምን ለማፍሰስ ወሬ የሚያቀብሉ በውስጥሽ አሉ፤ በኰረብታ ቤተ ጣዖት የተሠዋውን የሚበሉና ዝሙትን የሚፈጽሙ ሰዎች በመካከልሽ ይገኛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ አንዳንዶቹ ሌሎችን ለማስገደል ሐሰት ይናገራሉ፤ አንዳንዶቹ ለጣዖት የተሠዋውን ሁሉ ይመገባሉ፤ አንዳንዶቹ ዘወትር ፍትወታቸውን ለማርካት ይጣደፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውስጥሽ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ሌቦች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ፤ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፤ በመካከልሽም የማይገባ ነገርን አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደምን ያፈስሱ ዘንድ ቀማኞች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ፥ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፥ በመካከልሽ ሴሰኝነትን አደረጉ። |
በእነዚህ ነገሮች ሁሉ አስቆጣሽኝ እንጂ የልጅነትሽን ወራት አላስታወስሺም፤ ስለዚህ እነሆ እኔ ደግሞ መንገድሽን በራስሽ ላይ እመልሳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በርኩሰቶችሽ ሁሉ ላይ ሌላ ነውር አትጨምሪም።
እነርሱም በጥል ይቀርቡሻል፥ የድካምሽን ፍሬ ሁሉ ይወስዳሉ፥ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን አድርገውም ይተዉሻል፥ የዝሙትሽ ዕራቁትነት፥ ሴሰኝነትሽና ግልሙትናሽ ይገለጣል።
በርኩሰትሽ ሴሰኝነት አለ፥ መዓቴን በአንቺ ላይ እስክጨርስ ድረስ ከእንግዲህ ወዲያ ከርኩሰትሽ ንፁህ አትሆኚም ምክንያቱም አነጻሁሽ ነገር ግን ንፁህ አልሆንሺምና።
ወንዶችም ደግሞ ከአመንዝሮች ጋር አብረው ይሄዳሉና፥ በአማልክቶቻቸውም መቅደስ ከሚያመነዝሩ ሴቶች ጋር ይሠዋሉና ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማዊ በሆኑ ጊዜ፥ ምራቶቻችሁም ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም፤ የማያስተውልም ሕዝብ ይጠፋል።
በሰው ላይ እንደሚያደቡ ወንበዴዎች እንዲሁ ካህናት አብረው ተሰበሰቡ፥ ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ ላይ ይገድላሉ፤ በእርግጥም፥ ሴሰኝነትንም ያደርጋሉ።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
የቁባቴንም ሬሳ ከቈራረጥሁ በኋላ እያንዳንዱን ቁራጭ፥ እያንዳንዱ የእስራኤል ርስት ወዳለበት አገር ሰደድሁ፤ ይህን ያደረግሁትም ሰዎቹ በእስራኤል ዘንድ አሠቃቂና አስነዋሪ ድርጊት ስለፈጸሙ ነው።