Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 11:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በዚህች ከተማ ውስጥ የገደላችኋቸውን አብዝታችኋል፥ ጎዳናዎችዋንም በተገደሉት ሞልታችኋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በዚህች ከተማ ብዙ ሰው ገድላችኋል፤ መንገዶቿንም ሬሳ በሬሳ አድርጋችኋል።’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በዚህች ከተማ ብዙ ሰው ገድላችኋል፤ መንገዶችዋንም በሬሳ ሞላችኋቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በዚ​ህች ከተማ ውስጥ ግዳ​ዮ​ቻ​ች​ሁን አብ​ዝ​ታ​ች​ኋል፤ በጎ​ዳ​ና​ዎ​ች​ዋም ሙታ​ና​ች​ሁን ሞል​ታ​ች​ኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በዚህች ከተማ ውስጥ ግዳዮቻችሁንም አብዝታችኋል በጎዳናዎችዋም ግዳዮችን ሞልታችኋል።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 11:6
20 Referencias Cruzadas  

ምድር በደም ፍርድ ተሞልታለች፥ ከተማም በዓመፅ ተሞልታለችና፥ ሰንሰለት ሥራ።


በውስጧ ያሉ አለቆችዋ የገደሉትን እንደሚቦጫጭቁ ተኩላዎች ናቸው። ተገቢ ያልሆነ ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሳሉ፥ ነፍሶችንም ያጠፋሉ።


ደም ለማፍሰስ በአንቺ ውስጥ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽንም ጨቁነሽ የማይገባ ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ሐሜተኞች ሰዎች ደምን ሊያፈስሱ በአንቺ ውስጥ ነበሩ፥ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፥ በመካከልሽ ሴሰኝነትን አደረጉ።


እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤


በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው ጻድቅ ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርሳል።


በውስጧ የሚኖሩ ባለ ሥልጣኖቿ የሚያገሡ አንበሶች ናቸው፥ ፈራጆችዋም ለጠዋት ምንም የማያስቀሩ የማታ ተኩላዎች ናቸው።


ታማኝ ሰው ከምድሪቱ ጠፍቶአል፥ በሰው መካከል ቅን የለም፤ ሁሉም ለደም ያደባሉ፥ እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።


ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።


ሜም። የጻድቃንን ደም በውስጥዋ ስላፈሰሱ ስለ ነቢዮችዋ ኃጢአትና ስለ ካህናቶች በደል ነው።


ትሰርቃላችሁን፥ ትገድላላችሁን፥ ታመነዝራላችሁን፥ በሐሰትም ትምላላችሁን፥ ለበዓልም ታጥናላችሁን፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁን፤


መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ባትጨቊኑ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥ ክፉም እንዳይሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፥


እንዲሁም ሲምሱ አልያዝሻቸውም ነገር ግን በልብሶችሽ ላይ የንጹሐን ድሆች ደም ተገኝቶአል፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ብትፈጽሚም እንኳ


ልጆቻችሁን በከንቱ ቀሥፌአቸዋለሁ፤ ተግሣጽን አልተቀበሉም፤ ሰይፋችሁ እንደሚሰባብር አንበሳ ነብዮቻችሁን በልቶአል።


ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios