ለጌታ ቤት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰሎሞን የሚከተሉትን ዕቃዎች አሠራ፤ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ።
ዘፀአት 25:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገበታው ላይ ኅብስተ ገጹን ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማንኛውም ጊዜ በፊቴ እንዲሆን በገጸ ኅብስቱ በዚህ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠረጴዛውም በታቦቱ ፊት ለፊት ይቀመጥ፤ ለእኔ የሚቀርበው የተቀደሰ ኅብስት ዘወትር በጠረጴዛው ላይ መኖር አለበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገበታም ላይ ኅብስተ ገጹን ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገበታም ላይ የገጽ ኅብስት ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ። |
ለጌታ ቤት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰሎሞን የሚከተሉትን ዕቃዎች አሠራ፤ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ።
ደግሞም የተቀደሰ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም፥ ለእህል ቁርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በመለክያ ሁሉ ያገልግሉ ነበር።
በየጥዋቱና በየማታውም ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መዓዛው ያማረ ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የተቀደሰውንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የጌታን ትእዛዝ እንጠብቃለን፥ እናንተ ግን ትታችሁታል።
ሰሎሞንም እንዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፦ “ከአባቴ ከዳዊት ጋር እንዳደረግህ፥ የሚቀመጥበትንም ቤት ለመሥራት የዝግባ እንጨት እንደ ላክኽለት፥ እንዲሁ ለእኔ አድርግ።
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በጌታ ፊት መዓዛው ያማረውን ሽቶ ዕጣን ለማጠን፥ የተቀደሰውንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም በመባቻዎቹም በአምላካችንም በጌታ በዓላት ለማቅረብ ለአምላኬ ለጌታ ስም ቤት ልሠራለትና ልቀድስለት አሰብሁ።
ከእንጨት የተሠራው መሠዊያ ቁመቱ ሦስት ክንድ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ነበር፥ ማዕዘኖቹ፥ እግሩና ግድግዳው ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ እርሱም፦ “ይህ በጌታ ፊት ያለ ገበታ ነው” አለኝ።
“በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ ታቀርባላችሁ።” እናንተም፦ “ያረከስንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ። “የጌታ ገበታ የተናቀ ነው” በማለታችሁ ነው።
በተቀደሰው ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ሙዳዮችንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለመጠጥ ቁርባንም መንቀሎቹን ያስቀምጡበት፤ ሁልጊዜም የሚቀርበው እንጀራ በእርሱ ላይ ይሁን።
ዳዊትም “እንደተለመደው ሁሉ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ሴቶች ከእኛ ተጠብቀዋል፤ በተራ ተልእኮ ውስጥ እንኳ የሰዎቹ ዕቃዎች የተቀደሱ ናቸው፤ ዛሬማ ምንኛ የበለጠ ቅዱሳን መሆን ይገባቸዋል?” ሲል መለሰ።
ስለዚህ ካህኑ የተቀደሰውን እንጀራ ለዳዊት ሰጠው፤ ከጌታ ፊት ተነሥቶ በትኩስ እንጀራ ከተተካው ከኅብስት በስተቀር በዚያ ሌላ እንጀራ አልነበረምና።