ዘፀአት 21:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በፊታቸው የምታኖረው ሥርዓት ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በፊታቸው የምትደነግጋቸው ሥርዐቶች እነዚህ ናቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእስራኤላውያን የምትሰጣቸው ሕግ ይህ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በፊታቸው የምታደርገው ሥርዐት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊታቸው የምታደርገው ሥርዓት ይህ ነው። |
በከተሞቻቸውም ከተቀመጡት ከወንድሞቻቸሁ ዘንድ ስለ ደም መፋሰስ ስለ ሕግና ስለ ትእዛዝ ስለ ሥርዓትና ስለ ፍርድም ማናቸውም ጉዳይ ወደ እናንተ ቢመጣ ጌታን እንዳይበድሉ፥ ቁጣም በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳይመጣ አስጠንቅቁአቸው፤ እንዲህም ብታደርጉ በደለኞች አትሆኑም።
የቀሩት ሕዝብ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ በር ጠባቂዎቹ፥ መዘምራን፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ ከምድር ሕዝቦች ወደ እግዚአብሔር ሕግ ራሳቸውን የለዩ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉት ሁሉ፥
ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ፤ እናንተም የአገሩም ተወላጅ በእናንተም መካከል የሚኖር እንግዳ ርኩሰት ከሆኑት ከእነዚህ ማናቸውንም ነገር አታድርጉ፤
ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሕግና ሥርዓት ስሙ።
አንተ ግን እዚህ እኔ አጠገብ ቁም፤ እኔ በምሰጣቸው ምድር እነዚህን በመጠበቅ እንዲኖሩ፥ ሕግጋቴን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ እነግርሃለሁ።’
እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መመላለስ እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ ተቀብላችኋል፤ በእርግጥም እየተመላለሳችሁ ነው፤ ከዚህም በበለጠ አብዝታችሁ እንድታደርጉት በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችኋለንም።