Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 6:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 “ስለዚህ ስለምትሠራው ቤት ሕጎቼን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቴን ሁሉ ብትጠብቅ፥ ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል ለአንተ አጸናለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ስለምትሠራው ስለዚህ ቤተ መቅደስ ሥርዐቴን ብትከተል፣ ፍርዴን በተግባር ብትገልጸው፣ ትእዛዞቼን ብትጠብቅና ብትመላለስባቸው ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን ተስፋ በአንተ እፈጽመዋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12-13 “ሕጎቼን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቴን ሁሉ ብትጠብቅ፥ ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል ለአንተ አጸናለሁ፤ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ሆኜ አንተ በምትሠራው በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ እኖራለሁ። ከቶም አልለያቸውም።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “ስለ​ዚህ ስለ​ም​ት​ሠ​ራ​ልኝ ቤት በሥ​ር​ዐቴ ብት​ሄድ፥ ፍር​ዴ​ንም ብታ​ደ​ርግ፥ ትመ​ላ​ለ​ስ​ባ​ቸ​ውም ዘንድ ትእ​ዛ​ዞቼን ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ ለአ​ባ​ትህ ለዳ​ዊት የነ​ገ​ር​ሁ​ትን ቃል ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 “ስለዚህ ስለምትሠራው ቤት በሥርዐቴ ብትሄድ፥ ፍርዴንም ብታደርግ፥ ትመላለስበትም ዘንድ ትእዛዜን ሁሉ ብትጠብቅ፥ ለአባትህ ለዳዊት የነገርሁትን ቃል ከአንተ ጋር አጸናለሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 6:12
16 Referencias Cruzadas  

“ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን፥ ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ የምኖርበትን ቤተ መቅደስ የምትሠራልኝ አንተ ነህን?’


ምንም እንኳ ሌሎች አማልክትን እንዳይከተል ሰሎሞንን ቢከለክለውም፥ ሰሎሞን የጌታን ትእዛዝ አልጠበቀም፤


አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ብትሄድና ለእኔም ብትታዘዝ፥ ሕጌንና ትእዛዞቼንም ብትፈጽም ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ።”


የጌታ ቃል ወደ ሰሎሞንን እንዲህ ሲል መጣ፦


አሁንም የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ! ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት ‘አንተ በፊቴ ትሄድ እንደነበረው ልጆችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ፥ በፊቴም በቅንነት ቢመላለሱ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚነግሥ ልጅ መቼም አላሳጣህም’ ስትል የተናገርከውን የተስፋ ቃል ፈጽም!


እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፥ ልጅም ይሆነኛል፥ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ የመንግሥቱንም ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጸናለሁ።’


“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።


ልጆችህ ኪዳኔን፥ ይህንም የማስተማራቸውን ኪዳኔን ቢጠብቁ፥ ልጆቻቸው ደግሞ በዙፋንህ ላይ ለዘለዓለም ይቀመጣሉ።


መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥


“የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፤ እኔም በዚህ ስፍራ ከቆሙት ጋር ስፍራን እሰጥሃለሁ።”


ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት የምትጸኑ ከሆነ ነው፤ ይህም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፤ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos