አክዓብ፥ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኃጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቁጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም።
ዘዳግም 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከአንተ የበለጡትን እና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን ባስወጣልህ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር በሚያመጣህና ብዙዎችን ከአንተ የሚበልጡ ታላላቆችና ብርቱዎች የሆኑትን ሰባቱን አሕዛብ፦ ኬጢያውያንን፤ ጌርጌሳውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ በሚያስወጣቸው ጊዜ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር በሚያመጣህ ጊዜ በፊትህ ያሉትን ብዙ ሕዝቦች ያስወግድልሃል፤ እነርሱም ከአንተ በብዛትና በኀይል የሚበልጡት ሰባት የአሕዛብ ነገዶች ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩት ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከፊትህም ብዙና ታላላቅ አሕዛብን፥ ከአንተ የበለጡትን፥ የበረቱትንም ሰባቱን አሕዛብ፥ ኬጤዎናዊውን፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ከነዓናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ባወጣ ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን፥ ከአንተ የበለጡትን የበረቱትንም ሰባቱን አሕዛብ፥ ኬጢያዊውን ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ከነዓናዊውንም ፌርዛዊውንም ኤዊያዊውንም ኢያቡሳዊውንም ባወጣ ጊዜ፥ |
አክዓብ፥ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኃጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቁጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም።
እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ አለቆቹ ወደ እኔ ቀርበው፦ “የእስራኤል ሕዝብ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም እንደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ፌርዛውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞናውያን፥ ሞዓባውያን፥ ግብጻውያንና አሞራውያን ርኩሰት ያደርጋሉ እንጂ ከምድር ሕዝቦች እራሳቸውን አልለዩም፤
ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ እሰጣታለሁ ብዬ እጄን ወደ አነሳሁባት ምድር አመጣችኋለሁ፤ እርሷንም ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።’”
በደቡብም ምድር አማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮቹም ኬጢያዊና ኢያቡሳዊ አሞራዊም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ አጠገብ ተቀምጦአል።”
“ከግብጽ ያወጣህ አምላክህ ጌታ ከአንተ ጋር ነውና፥ ጠላቶችህን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄድ፥ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ከአንተ የሚበልጥ ሠራዊትንም በምታይበት ጊዜ አትፍራቸው።
ወተትና ማር ወደምታፈሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ባመጣኋቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፥ ከበለጸጉም በኋላ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ።
ጌታ አምላክህም ራሱ በፊትህ ቀድሞ ይሄዳል፤ እነዚህንም አሕዛብ ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ምድራቸውን ትወርሳለህ፤ ጌታ እንደ ተናገረው ኢያሱም አንተን ቀድሞ ይሻገራል።
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ፥ ከእናንተ የበረቱትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊታችሁ እንዲያስወጣ፥ እናንተንም እንዲያስገባ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ይሰጣችሁ ዘንድ ነው።
“ጌታ አምላክህ ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ፥ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ባስገባህ ጊዜ፥ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥
“እስራኤል ሆይ፥ ስማ! ከአንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ እስከ ሰማይም ድረስ የተመሸጉትን ታላላቅ ከተሞች ለመውረስ እንድትገቡ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገረዋለህ።
እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊትህ ዛሬ የሚያልፈው ጌታ እግዚአብሔር መሆኑን እወቅ፥ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ ጌታ ተስፋ እንደሰጠህ አንተም ታሳድዳቸዋለህ፥ በፍጥነትም ታጠፋቸዋለህ።
“ጌታ አምላክህ ከፊትህ ካስወጣቸው በኋላ፥ በልብህ፥ ‘እንድንወርሳት ወደዚች ምድር ጌታ ያስገባኝ በጽድቄ ምክንያት ነው’ አትበል፤ ጌታ እነዚህን ሕዝቦች ከፊትህ ያስወጣቸው ስለ ኃጢአታቸው ነው።
በምሥራቅና በምዕራብም ወዳለው ወደ ከነዓናዊው፥ ወደ አሞራዊውም፥ ወደ ኬጢያዊውም፥ ወደ ፌርዛዊውም፥ በተራራማውም አገር ወዳለው ወደ ኢያቡሳዊው፥ ከአርሞንዔምም በታች በምጽጳ ወዳለው ወደ ኤዊያዊው ላከ።
ዮርዳኖስንም ተሻገራችሁ፥ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ፤ የኢያሪኮም ሰዎች፥ አሞራዊው፥ ፌርዛዊው፥ ከነዓናዊው፥ ኬጢያዊው፥ ጌርጌሳዊው፥ ኤዊያዊው፥ ኢያቡሳዊው ተዋጉአችሁ፤ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋቸው።
ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደሆነ፥ እርሱም ከነዓናዊውን ኬጢያዊውንም ኤዊያዊውንም ፌርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ከፊታችሁ ፈፅሞ እንደሚያሳድድ በዚህ ታውቃላችሁ።