ዕዝራ 9:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ አለቆቹ ወደ እኔ ቀርበው፦ “የእስራኤል ሕዝብ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም እንደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ፌርዛውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞናውያን፥ ሞዓባውያን፥ ግብጻውያንና አሞራውያን ርኩሰት ያደርጋሉ እንጂ ከምድር ሕዝቦች እራሳቸውን አልለዩም፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ መሪዎቹ ወደ እኔ መጥተው እንዲህ አሉኝ፤ “ካህናቱንና ሌዋውያኑን ጨምሮ የእስራኤል ሕዝብ ከጎረቤቶቻቸው ከከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኢያቡሳውያን፣ ከአሞናውያን፣ ከሞዓባውያን፣ ከግብጻውያንና ከአሞራውያን ርኩሰት ራሳቸውን አልለዩም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ይህም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ መሪዎች አንዳንዶቹ ወደ እኔ ቀርበው ከዚህ የሚከተለውን ቃል ነገሩኝ፦ “ሕዝቡና ካህናቱ ሌዋውያኑም ጭምር በጐረቤት ባሉት በዐሞን፥ በሞአብና በግብጽ ከሚኖሩትና እንዲሁም ከከነዓናውያን፥ ከሒታውያን፥ ከፈሪዛውያን፥ ከኢያቡሳውያንና ከአሞራውያን ርኲሰት ራሳቸውን አልጠበቁም፤ እነዚያ አሕዛብ ሲፈጽሙት የነበረውን አጸያፊ ነገር ሁሉ አድርገዋል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ይህም ከተፈጸመ በኋላ የሕዝቡ አለቆች ወደ እኔ ቀርበው፥ “የእስራኤል ሕዝብ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ እንደ ከነዓናውያን፥ እንደ ኬጤዎናውያን፥ እንደ ፌርዜዎናውያን፦ እንደ ኢያቡሴዎናውያን፥ እንደ አሞናውያን፥ እንደ ሞዓባውያን፥ እንደ ግብፃውያንና እንደ አሞራውያን ርኵሰት ያደርጋሉ እንጂ ከምድር አሕዛብ አልተለዩም፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ይህም ከተፈጸመ በኋላ አለቆቹ ወደ እኔ ቀርበው፦ “የእስራኤል ሕዝብ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ እንደ ከነዓናውያን፥ እንደ ኬጢያውያን፥ እንደ ፌርዛውያን፥ እንደ ኢያቡሳውያን፥ እንደ አሞናውያን፥ እንደ ሞዓባውያን፥ እንደ ግብጻውያንና እንደ አሞራውያን ርኵሰት ያደርጋሉ እንጂ ከምድር አሕዛብ አልተለዩም፤ Ver Capítulo |