Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 9:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “እስራኤል ሆይ፥ ስማ! ከአንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ እስከ ሰማይም ድረስ የተመሸጉትን ታላላቅ ከተሞች ለመውረስ እንድትገቡ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገረዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እስራኤል ሆይ፤ ስማ፤ ሰማይ ጠቀስ ቅጥር ያላቸው ታላላቅ ከተሞች ያሏቸውን፣ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ አስለቅቀህ ለመግባት ዮርዳኖስን አሁን ትሻገራለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! አድምጥ፤ ከአንተ የሚበልጡትንና በኀይልም ብርቱ የሆኑትን የአሕዛብ ምድርና ቅጽሮቻቸው እስከ ሰማይ የደረሱ ታላላቅ ከተሞቻቸውን ለመውረስ ትገባ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገራለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ት​ንና የበ​ረ​ቱ​ትን አሕ​ዛብ፥ የቅ​ጽ​ራ​ቸው ግንብ እስከ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ታላ​ላ​ቆች ከተ​ሞ​ችን ለመ​ው​ረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ረ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ እስከ ሰማይም ድረስ የተመሸጉትን ታላላቆች ከተሞች ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገረዋለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 9:1
24 Referencias Cruzadas  

እንዲህም፦ “ኑ ለእኛ ከተማ እንመስርት፥ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበታተንም ስማችንን እናስጠራ” አሉ።


ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው፦ “ይህ ከግብጽ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅም፤ ስለዚህ ተነሥና በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን” አሉት።


“እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ባሉጥ ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው ደመሰስሁ፤ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።


በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብጽ ካለችው ከጣኔዎእ ከሰባት ዓመት በፊት የተቈረቈረች ከተማ ነበረች።


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ወደ ከነዓን ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥


ወዴትስ እንወጣለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል፥ ከተሞቹም ታላላቆች የተመሸጉም እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፥’ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አወኩት።


ከዚያም ጌታ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል፤ እናንተም፥ ከእናንተ ይልቅ ታላላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ታስለቅቃላችሁ።


አምላካችሁ ጌታ በሚሰጣችሁ ምድር ትገቡባትና ትወርሷት ዘንድ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ስለሆነ፥ ምድሪቱን ወርሳችሁ በምትኖሩባት ጊዜ፥


ጌታ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁምና በኖራም ምረጋቸው።


በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ “ጌታ አምላካችሁ ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ የእናንተ ጦር ሰዎች ሁሉ ታጥቀው በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።


“አሁንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው በሕይወትም እንድትኖሩ፥ የአባቶቻችሁም አምላክ ጌታ ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ የማስተምራችሁን ሥርዓትና ሕግጋት ስሙ።


ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ፥ ከእናንተ የበረቱትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊታችሁ እንዲያስወጣ፥ እናንተንም እንዲያስገባ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ይሰጣችሁ ዘንድ ነው።


“ጌታ አምላክህ ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ፥ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ባስገባህ ጊዜ፥ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥


“ጌታ አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከአንተ የበለጡትን እና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን ባስወጣልህ ጊዜ፥


“በሰፈሩ መካከል እለፉ፥ ሕዝቡንም እንዲህ ብላችሁ እዘዙ፦ ‘ጌታ አምላካችሁ ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ምድር በሦስት ቀን ውስጥ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ልትወርሱአት ትገቡባታላችሁና ስንቃችሁን አዘጋጁ።’ ”


ጌታ እናንተን እንዳሳረፋችሁ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ ጌታ አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ፤ ከዚያም በኋላ የጌታ ባርያ ሙሴ በፀሐይ መውጫ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ትመለሳላችሁ ትወርሱዋታላችሁም።”


አሁን እንግዲህ በዚያን ቀን ጌታ የተናገረውን ይህን ተራራማ አገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔናቃውያን ታላላቆችና የተመሸጉ ከተሞችም በዚያ እንዳሉ ሰምተህ ነበር፤ ምናልባት ጌታ ከእኔ ጋር ይሆናል፥ ጌታም እንደ ተናገረኝ አሳድዳቸዋለሁ።”


እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ሊሻገሩ ከየድንኳናቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር።


ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።


ኢያሱም ካህናቱን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ በሕዝቡ ፊት እለፉ፤” እነርሱም የቃል ኪዳኑንም ታቦት ተሸክመው በሕዝቡ ፊት ሄዱ።


ሕዝቡም በመጀመሪያው ወር በአሥረኛው ቀን ከዮርዳኖስ ወጡ፥ በኢያሪኮም ዳርቻ በምሥራቅ በኩል በጌልገላ ሰፈሩ።


ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “በአምላካችሁ በጌታ ታቦት ፊት በዮርዳኖስ መካከል እለፉ፤ ከእናንተም ሰው ሁሉ በእስራኤል ልጆች ነገድ ቍጥር በትከሻው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos