Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 16:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 አክዓብ፥ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኃጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቁጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን ኀጢአት እንደ ቀላል ነገር ከመቍጠሩም በላይ የሲዶናውያንን ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በኣልን አመለከ፤ ሰገደለትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 አክዓብ፥ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኃጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቊጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 በና​ባ​ጥም ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት መሄድ አል​በ​ቃ​ውም፤ የሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ን​ንም ንጉሥ የኤ​ያ​ት​ባ​ሔ​ልን ልጅ ኤል​ዛ​ቤ​ልን አገባ፤ ሄዶም በዓ​ልን አመ​ለከ ሰገ​ደ​ለ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት መሄድ ታናሽ ነገር መሰለው፤ የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በኣልን አመለከ፤ ሰገደለትም።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 16:31
35 Referencias Cruzadas  

“የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ” አለቻት። እርሷም፦ “ባሌን መውሰድሽ በውኑ ጥቂት ነገር ነውን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም፦ “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይተኛ” አለች።


የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፥ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።


ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!


ይልቅስ አሁን እስራኤላውያንን ሁሉ እንዳገኛቸው በቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብልኝ፤ በንግሥት ኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያትንና አራት መቶ የአሼራ ነቢያትን ጭምር ይዘህ ና።”


ኤልዛቤል የጌታን ነቢያት ታስገድል በነበረችበትም ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ፥ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ ይመግባቸው ነበር።


ኢዩ የሰማርያን ሕዝብ በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ንጉሥ አክዓብ በዓልን ያገለገለው በመጠኑ ነበር፤ እኔ ግን ከእርሱ ይበልጥ ላገለግለው እፈልጋለሁ፤


የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ በመጣስ የሚሰግዱላቸውን ከወርቅ የተሠሩ ሁለት ጥጆችን አቆሙ፤ እንዲሁም አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሠሩ፤ ለከዋክብት ሰገዱ፤ በዓል ተብሎ ለሚጠራውም ባዕድ አምላክ አገልጋዮች ሆኑ።


ምናሴ አባቱ ሕዝቅያስ ደምስሶአቸው የነበሩትን የአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች እንደገና እንዲሠሩ አደረገ፤ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ባደረገውም ዓይነት በዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ መሠዊያዎችን፥ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስልን ሠራ፤ የሰማይ ከዋክብትንም አመለከ።


እርሱም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ ይሁን እንጂ እርሱ የአባቱንና የእናቱን የኤልዛቤልን ያኽል መጥፎ ሰው አልነበረም፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውን ባዕድ አምላክ ለማምለክ አባቱ አሠርቶት የነበረውን ምስል አስወገደ፤


ነገር ግን የአባቱን አምላክ ፈለገ፥ በትእዛዙም ሄደ፥ እንደ እስራኤልም ያለ ሥራ አልሠራም።


በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ግን ሄደሃልና፥ የአክዓብም ቤት እንዳደረገ ይሁዳንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እንዲያመነዝሩ አድርገሃልና፥ ከአንተም የሚሻሉትን የአባትህን ቤት ወንድሞችህን ገድለሃልና፥


ኢሳይያስም እንዲህ አለ፤ “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፤ ስሙ፤ የሰውን ትዕግሥት መፈታተናችሁ አንሶ የአምላኬን ትዕግሥት ትፈታተናላችሁን?


ለእኔ የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወስደሽ ለእነርሱ መብል እንዲሆኑ ሠዋሻቸው። አመንዝራነትሽ አንሶ ነውን?


አንቺ በእነርሱ መንገድ መሄድሽና ርኩሰታቸውንም መከተልሽ ብቻ ሳይሆን፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመንገድሽ ሁሉ ከእነርሱ የበለጠ ምግባረ ብልሹ ነበርሽ።


የቀረውን ማሰማርያችሁን በእግራችሁ የረገጣችሁት፥ በመልካሙ ማሰማርያ መሰማራታችሁ ባይበቃችሁ ነውን? የቀረውንስ ውኃ በእግራችሁ ያደፈረሳችሁት፥ ጥሩውን ውኃ መጠጣታችሁ ባይበቃችሁ ነውን?


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ ይህን አይተሃልን? በዚህ የሰሩትን ርኩሰት ሊያደርጉ ለይሁዳ ቤት ይህ ቀላል ነገር ነውን? ምድሪቱን በዓመፅ ሞልተዋታል፥ ሊያስቆጡኝም ተመልሰዋል፥ እነሆ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫቸው አቅርበዋል።


በበኣሊም የበዓል ቀኖች ዕጣን ለእነርሱ በማጠንዋና ራስዋን በጉትቾችዋና በጌጥዋ በማስጌጥ ውሽሞችዋን ተከትላ እኔን በመርሳትዋ እቀጣታለሁ፥ ይላል ጌታ።


የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር የለያችሁ፥ የጌታንም ማደሪያ አገልግሎት እንድትሠሩ፥ እንድታገለግሉአቸውም በማኅበሩ ፊት እንድትቆሙ ወደ እርሱ ለማቅረብ መፍቀዱን እንደ ቀላል ነገር ቈጠራችሁትን?


“ጌታ አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከአንተ የበለጡትን እና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን ባስወጣልህ ጊዜ፥


ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን፥ ባርያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ስለምትላት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤


አሴርም በዓኮ፥ በሲዶን፥ በአሕላብ፥ በአክዚብ፥ በሒልባ፥ በኣፌቅና በረአብ የሚኖሩትን ሕዝብ በምድሪቱ ካሉት ከነዓናውያን ጋር አብረው ኖሩ።


ሲዶናውያን፥ አማሌቃውያንና ማዖናውያን አሠቃዩአችሁ፤ እናንተም እንድረዳችሁ ወደ እኔ ጮኻችሁ፤ ታዲያ እኔ ከእጃቸው አላዳንኋችሁምን?


እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የሶሪያን፥ የሲዶናን፥ የሞዓብን፥ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን ጌታን ስለተዉና ስላላገለገሉት፥


ስለዚህ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ስጋት በጸጥታ እንደሚኖሩ ሁሉ፥ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለ መኖሩ ሕዝቡ ባለጸጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፥ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ግንኙነት አልነበረውም።


ከዚያም እስራኤላውያን በጌታ ፊት ክፉ ነገር አደረጉ፤ የበኣል አማልክትንም አመለኩ።


እስራኤላውያን በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ አምላካቸውን ጌታንም ረሱ፤ በኣልንና አስታሮትን አመለኩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos